በአርቲስትና የመብት ተሟጋች ታማኝ በየነ የሚመራው ግብረ ሰናይ ድርጅት የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡

መረጃ ቲቪን ሰብስክራይብ በማድረግ ወቅታዊ ዜናዎችን፣ ትንተናዎችን፣ የኪነጥበብ ፕሮግራሞችን እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ማግኘት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

‘ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት’ የተሰኘው ግብረ ሰናይ ድርጅት የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል 11 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የሚገመት ሕክምና ቁሳቁስ ለኢትዮጵያ ድጋፍ አድርጓል፡፡
በአሜሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተመሥርቶ በአርቲስትና የመብት ተሟጋች ታማኝ በየነ የሚመራው ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያግዙ 11 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ የሕክምና ቁሳቁስ ለጤና ሚኒስቴር አስረክቧል፡፡
ድጋፉንም የጤና ሚኒስቴር ሚንስትር ሊያ ታደሰ (ዶክተር) ዛሬ ተረክበዋል፡፡ ድጋፉ በሀገር ዓቀፍ ደረጃ ወረርሽኙን ለመከላከል እየተደረገ ያለውን ጥረት የሚያበረታታ በመሆኑ ዶክተር ሊያ ለጋሾችን አመሥግነዋል፡፡ ድጋፉን አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
(አብመድ)