በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ክትባትም ሆነ መድሃኒት አልተገኘም፡፡

SHEGER FM 102.1 RADIO የኮሮና ቫይረሰ ወረርሽኝን ለመከላከል የተለያዩ አገራት በምርምር ቤታቸው እየባተሉ ቢሆንም እስከ ዛሬ ድረስ መድሃኒትም ሆነ ክትባት አግኝቻለሁ ብሎ ያወጀ አንድም አገር የለም፡፡በኢትዮጵያም የኮሮና ቫይረስ ክትባትም ሆነ መድሃኒት አልተገኘም፡፡

የቴክኖሎጂና የኢኖቬሽን ሚኒስቴር ትናንት የሰጠውን መግለጫ በመሰረታዊ መልኩ ቀይሮታል፡፡
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ይህንኑ ወረርሽኝ ለመከላከል የተገኘው መላ ተደጋጋሚ የምርምር ሂደት አልፎ ወደ ምርት ይሻገራል ማለቱን ትናንት ተናግሯል፡፡
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ይህንን ሲናገርም፤ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በበኩላቸው ምርመሩ በመድሃኒት ግኝት ሂደት መመሪያ መሰረት ብዙ የምርምር ሂደቶች የሚቀሩት ነው ብለዋል፡፡
ታዲያ ይህ ሁሉ ደረጃ እና ጊዜ የሚወስድ ከሆነ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መድሃኒቱ የመከላከል አቅም የሚጨምር፣ መርዛማነት የሌለው እና አዋጭነቱ የተረጋገጠ ነው ማለቱ ትክክል ነው ወይ ብለን የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን ጠይቀናል፡፡
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርም የምርምር ሂደቱ ተጠናክሮ ወደ ምርት ለመግባት ዝግጅት እየተደረገ ነው የሚለውን ዐረፍተ ነገር ማስተካከሉን አስረድቷል፡፡
ዶ/ር ሊያ ይሄው የምርምር ውጤት ወደፊት በሚደረጉ የእንስሳት እና የክሊኒካል ምርምሮች በዓለም አቀፍ እና ሀገር በቀል ባለሙያዎች ይካሄዳል ብለዋል፡፡
ጤና ሚኒስትሯ የዛሬን ችግር ለመፍታት የምንከተለው ብቸኛ አማራጭ በመንግስት እና በጤና ሚኒስቴር የሚወሰዱትን እርምጃዎች እና የተሰጡትን የጤና ምክሮችን በመተግበር መሆኑን አሳስበዋል፡፡
ማስተካከያውም ወደ ቀጣይ የምርት ሳይሆን የምርምር ሂደት ለመግባት ዝግጅት እየተደረገ ነው የሚል ነው፡፡
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የተለያዩ ሀገራት በምርምር ቤታቸው እየተጉ ቢሆንም እስከዛሬ ድረስ መድሃኒትም ሆነ ክትባት አግኝቻለሁ ብሎ ያወጀ አንድም ሀገር የለም፡፡
በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ክትባትም ሆነ መድሃኒት አልተገኘም፡፡