ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መንገደኞች በጊዮን ሆቴል ችግሩን በበቂ ሁኔታ ለመቋቋም አስቸጋሪ ሁኔታዎችን ኢሰመጉ ታዝቧል

መረጃ ቲቪን ሰብስክራይብ በማድረግ ወቅታዊ ዜናዎችን፣ ትንተናዎችን፣ የኪነጥበብ ፕሮግራሞችን እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ማግኘት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

* በጊዮን ሆቴል ችግሩን በበቂ ሁኔታ ለመቋቋም አስቸጋሪ ሁኔታዎችን ታዝቧል።
– የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ
የኮሮና ቫይረስ ሥርጭትን ለመቆጣጠር የሚደረገው ጥረት ሰብዓዊ መብቶችን በማይጥስ መልኩ መሆን ይገባዋል!
የኮሮና ቫይረስ ሥርጭትን ለመቆጣጠር እና እያደረሰ ያለውን ጉዳት ለመቀነስ መንግሥት እየወሰዳቸው ከሚገኙ እርምጃዎች መካከል ከውጭ አገራት የሚገቡ መንገደኞችን ከማኅበረሰቡ ጋር ሳይቀላቀሉ ለተወሰኑ ቀናት ለይቶ ማቆየት አንዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከውጭ ሐገራት ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መንገደኞች ተለይተው ከሚቆዩባቸው ሥፍራዎች መካከል አንዱ በሆነው የአዲስ አበባ ግዮን ሆቴል ኢሰመጉ ምልከታ ያደረገ ሲሆን በዚህም ችግሩን በበቂ ሁኔታ ለመቋቋም አስቸጋሪ የሆኑ ሁኔታዎችን ታዝቧል።