የአምባሳደሮች ምደብ ቦታ ይፋ ተደረገ

የክቡራን አምባሳደሮች ምደብ ቦታ ይፋ ተደረገ
===========================
የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ ኢትዮጵያን በተለያዩ አገራት የሚወክሉ 15 አዳዲሰ አምባሳደሮችን ሹመት የካቲት 24 ቀን 2012 ዓም ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል። በዚሁ መሰረት ክቡራን አምባሳደሮቹ የሚመደቡባቸው አገራት ከዚህ በሚከተለው መሰረት ተወስኗል።
ክቡራን ባለሙሉስልጣን አምባሳደሮች
=======================
1. ክቡር አምባሳደር ብርሁኑ ፀጋዬ አውስትራሊያ ካንቤራ
2. ክብርት አምባሳደር ያለም ፀጋይ ኩባ ሃቫና
3. ክብርት አምባሳደር ሂሩት ዘመነ ቤልጄም ብራሰልስ
4. ክቡር አምባሳደር ዶ/ር ማርቆስ ተክሌ ግብጽ ካይሮ
5. ክቡር አምባሳደር ባጫ ጊና ሞሮኮ ራባት
6. ክቡር አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ሱዳን ካርቱም
7. ክቡር አምባሳደር ምህረታብ ሙሉጌታ ኤርትራ አስመራ
8. ክቡር አምባሳደር ነብያት ጌታቸው አልጀሪያ አልጀርስ እንዲሁም
9. ክቡር አምባሳደር ተፈሪ መለስ እንግሊዝ ለንደን ሆነው እንዲሰሩ ተመድበዋል። እንዲሁም
ክቡራን አምባሳደሮች
============
1. ክቡር አምባሳደር አድጎ አምሳያ ስዊድን ስቶክሆልም ምክትል ሚሲዮን መሪ
2. ክቡር አምባሳደር ጀማል በከር ባህሬን ማናማ ቆንስል ጄኔራል
3. ክቡር አምባሳደር አብዱ ያሲን ሳኡዲ አረቢያ ጄዳ ቆንስል ጄኔራል
4. ክቡር አምባሳደር ለገሠ ገረመው ካናዳ ኦታዋ ምክትል ሚሰዮን መሪ
5. ክብርት አምባሳደር እየሩሳሌም አምደማርያም የተባበሩት አረብ ኢሚሪቶች ዱባይ ቆንስል ጄኔራል
6. ክቡር አምባሳደር ሽብሩ ማሞ አሜሪካ ሚኒሶታ ቆንስል ጄኔራል ሆነው እንዲሰሩ ተመድበዋል።
ክቡራን አምባሳደሮቹ በተመደቡባቸው አገራት የፕሮቶኮል አሰራር መሰረት አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ተጠናቅቆ በቅርቡ ወደ ምድብ ቦታቸው ተንቀሳቅሰው ስራቸውን በይፋ የሚጀምሩ ይሆናል።