የትግራይ ክልላዊ መንግስት የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ደነገገ፡፡


ኢትዮጵያን ካጋጠሟት እጅግ ውስብስብ ችግሮች ለማዳን የተለያዩ ጠቃሚ ሃሳቦችን እና ገንቢ ትችቶችን የሚያቀርቡ ነፃ ሚዲያዎች ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ይታወቃል። ስለዚህም ኢትዮ360፣ መረጃ ቲቪ፣ አዲስ ድምጽ፣ ምንሊክ ቲቪ እና ሌሎችም የኢትዮጵያዊነት አጀንዳ የሚያራምዱ ሚዲያዎች በመተባበር ፕሮግራሞቻቸውን በሳተላይት ቲቪ ለኢትዮጵያ ህዝብ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ሚዲያዎች የፈጠሩት ማህበር የሳተላይት ወጪውን መሸፈን እንዲያስችለው ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ ከፍተናል → እዚህ ሊንክ ላይ ይጫኑ። ለትብብርዎ እናመሰግናለን።
የትግራይ ክልላዊ መንግስት የኮረና ተሐዋሲ ወረርሺኝን ለመግታት የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ደነገገ፡፡
የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ከዛሬ ጀምሮ መተግበር የጀመረ ሲሆን፣ ከመጋቢት 19 ቀን 2012 ዓ.ም በኋላ ባለው ደግሞ ከቦታ ወደ ቦታ መንቀሳቀስን ገድቦ ለሁለት ሳምንታት ይዘልቃል ተብሏል፡፡ አዋጁ በሰዎች ከቦታ ወደ ቦታ የመንቀሳቀስ፣ በመንግስትም ኾነ በግል ሥራና አገልግሎት፣ ንግድ ተቋማትና ማኅበራዊ ጉዳዮች ዙርያ ሙሉ በሙሉ፣ እንዲሁም በከፊል ክልከላዎች የሚያኖር ነው፡፡
የክልሉ መንግስት ኮሚውኒኬሽን ቢሮ መረጃ እንደሚያመለክተው የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ በትግራይ ክልል ሕገ መንግስት አንቀጽ 56 ንኡስ አንቀጽ 8 እንዲሁም አንቀጽ 103 ንኡስ አንቀጽ 1 መሰረት በክልሉ ሥራ አስፈፃሚ ካቢኔ ፀድቆ የተደነገገ ነው ተብሏል፡፡
የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በሰጡት መግለጫ፦ በትግራይ በተወሰነው የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ መሰረት ከገጠር ወደ ከተማ፣ ከከተማ ወደ ገጠር፣ ከከተማ ወደ ከተማ የሚደረግ እንቅስቃሴ ለሁለት ሳምንት መታገዱን ዐስታውቀዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ሕዝብ የሚሰበሰብባቸው ትላልቅ ገበያዎች፣ እንደ ሰርግ፣ ተዝካር እና የመሳሰሉ ሌሎች ማኅበራዊ ስነ ስርዓቶች በአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ታግደዋል፡፡ የክልሉ መንግስት ሠራተኞችን በተመለከተ እንደየስራቸው ሁኔታ ሙሉ በሙሉ እንዲያርፋ፣ ቤታቸው ኾነው እንዲሰሩና በመደበኛ አካሄድ ስራቸውን የሚከውኑበት አካሄዱ መኖሩንም ገልጿል።
አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የሚተላለፍ ማንኛውም አካል እስከ ሁለት ዓመት የሚዘልቅ ቅጣት እንደሚጠብቀው የትግራይ ክልል መንግስት ዐስታውቋል፡፡