ቋሚ ሲኖዶስ: የኮሮና ቫይረስን መስፋፋት ለመግታት፥ የትምህርት ተቋሞች ሙሉ በሙሉ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ መምሪያዎች እና የአህጉረ ስብከት ጽ/ቤቶች በከፊል እንዲዘጉ ወሰነ

ለአስቸኳይ ሥራ ከሚፈለጉት እና ጥሪ ሲደረግላቸው ከሚመጡት በቀር፥ መላው የጠቅላይ ቤተ ክህነት እና የአህጉረ ስብከት ጽ/ቤቶች ሠራተኞች፣ ሥራቸውን በየቤታቸው እያከናወኑ ይቆያሉ፤ የአብነት ት/ቤቶች እና ሙዓለ ሕፃናት፣ የካህናት ማሠልጠኛዎች፣ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲዎች እና ኮሌጆች፥ የመማር ማስተማር ሥራቸውን ላልተወሰነ ጊዜ ሙሉ በሙሉ ያቆማሉ፤ ደቀ መዛሙርት እና ተማሪዎች፥ የተማሩትን በየቤታቸው እየቀጸሉ እና እያጠኑ ይሰነብታሉ፤ የመንበረ ፓትርያርክ ቅርሳቅርስ መምሪያ እና …