ከኮሮና ወረርሽኝ ያገገመችዉ ቻይና

በጎርጎረሳዉያኑ 2019 መጠናቀቅያ ቻይና ዉስጥ የተቀሰቀሰዉ የኮሮና ወረርሽ በአሁኑ ወቅት ዓለምን አዳርሶአል። በቻይና የኮሮና ስርጭትን ለመግታት ጠንካራ የዝዉዉር እገዳ  ከተጣለ እና ኤኮኖሚያዊ ገቢን የሚያስገኙ ማኅበራዊ መስተጋብሮች ሁሉ ሙሉ ከተዘጉ በኋላ ዛሬ ኮሮና በሚያስከትለዉ በሽታ የሚሞተዉም ሆነ የሚለከፈዉ ሰዉ ቁጥር በመቀነሱ ተነግሮአል።…