" /> የኢትዮጵያ አየር መንገድ 260 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ ሊደርስበት ይችላል ተብሏል | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 260 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ ሊደርስበት ይችላል ተብሏል

Image result for ethiopian airlines lossesEthiopian Airlines negotiating with its suppliers for price reduction

የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ያደረገው ጥናት አየር መንገዱ 260 ሚሊዮን ዶላር ሊያጣ እንደሚችል ተናግሯል የኢትዮጲያ አየር መንገድ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት አሁን እያጋጠመው ያለውን የገቢ መቀነስ ለመቆጣጠር እና የሚያመጣበትን ጉዳት ለመቀነስ ሌሎች አገልግሎት አቅራቢያዎች የዋጋ ቅነሳ እና ማሻሻያ እንዲያደርጉ ጠየቀ፡፡

Due to the expanding range and impact of the corona virus- covid19 on the economic and social crises worldwide, the star alliance member Ethiopian air lines starts to negotiate with its suppliers and service providers for a discount. In an email sent to its suppliers the airline is asking to be provided with discount on all materials supplied by companies by way of concession, volume or monetary amount to minimize the impact and survive the business.
የኢትዮጵያ አጠቃላይ ኢኮኖሚ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት መፈተን እንደጀመረ ተሰምቷል፡፡ አገሪቱ በህጋዊ መንገድ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የምታገኝበት (ሬምታንስ) እንደቀነሰ፣ የገቢና ወጪ ንግድ መዳከም እንደጀመረ የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ተናግሯል፡፡የኢትዮጵያ አየር መንገድም በዚሁ ወረርሽኝ 190 ሚሊየን ዶላር ማጣቱን ቢናገርም፣ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ያደረገው ጥናት አየር መንገዱ 260 ሚሊዮን ዶላር ሊያጣ እንደሚችል ተናግሯል፡፡
የኢትዮጲያ አየር መንገድ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት አሁን እያጋጠመው ያለውን የገቢ መቀነስ ለመቆጣጠር እና የሚያመጣበትን ጉዳት ለመቀነስ ሌሎች አገልግሎት አቅራቢያዎች የዋጋ ቅነሳ እና ማሻሻያ እንዲያደርጉ ጠየቀ፡፡ አየር መንገዱ በአሁኑ ሰዓት 190 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማጣቱን ሲገልፅ ጉዳቱን ለመቀነስ የተለያዩ አማራጮችን እየወሰደ ይገኛል፡፡ ባለፈው ሳምንት የተባበሩት መንግስታት ኢኮኒሚክ ኮሚሽን ባወጣው ሪፖርት አየር መንገዱ እስከ 260 ሚሊዮን ዶላር ሊያጣ እንደሚችል ገልፁል፡፡ በሳለፍነው ሳምንት አየር መንገዱ ለሰራተኞቹ ያላቸውን የአመት ፈቃድ ቶሎ ቶሎ ወስደው እንዲጠቀሙ ማሳሰቡ ይታወሳል፡፡ ይህም የተሻለ የስራ ጊዜ ሲመጣ አየር መንገዱ በሙሉ አቅሙ እንዲሰራ ይረዳዋል ተብሏል፡፡

 


የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV