" /> በወለጋ ጦርነት ባለፉት ሳምንታት ከ30 በላይ ሰዎች ተገድለዋል፤ ነዋሪዎች ወደ አሶሳ፣ ቡራዩና ጋምቤላ ሸሽተዋል | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

በወለጋ ጦርነት ባለፉት ሳምንታት ከ30 በላይ ሰዎች ተገድለዋል፤ ነዋሪዎች ወደ አሶሳ፣ ቡራዩና ጋምቤላ ሸሽተዋል

ዶይቼ ቬለ – በቄለም ወለጋ ዞን ወረዳዎች በጸጥታ ኃይሎች እና በሸመቂዎች መካከል በሚደረጉ ግጭቶችን ነዋሪዎች ወደ አሶሳ፣ ቡራዩና ጋምቤላ መሸሻቸውን ተናገሩ፡፡ በተለይም ባለፉት ሁለት ወራት በዞኑ በሚገኙት ሳዮ፣ ሐዋ ገላን፣ አንፊሎ እና መቻራ በተባሉ አካባበዎች ከ30 በላይ ሰዎች በታጠቂዎችና መንግሥት ጸጥታ ኃይሎች መገደላቸውን ነዋሪዎቹ ገልጸዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ኮምዩንኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ከአካባቢው የሸሹ ነዋሪዎች መኖራቸውን ለዶይቼ ቬለ አረጋግጠዋል።
ከቄለም ወለጋ ዞን ደንቢ ዶሎ ከተማ በ25 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ የምትገኘው ሳዩ ወረዳ ነዋሪ መሆናቸውን እና በአሁኑ ጊዜ በታጣቂዎችና በመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች መካከል ያለው ግጭቶችን በመሸሽ ወደ ጋምቤላ ከተማ መሄዳቸውን የነገሩን የአካባቢው ነዋሪ በሳዩ ወረዳ ከጥር ወር ጀምሮ በነበሩተደጋጋሚ ግጭቶች 30 የሚደርሱ ሰዎች ሞሞታውን ገልጸዋል፡፡ በአካባው የሚገኘው የመንግስት ጸጥታ ኃይሎች ታጠቂዎች ያሉበት ስፍራ ንገሩት በማለት ጥቃት እንዲሚፈጽሙና በጫካ የሚኖሩ የታጠቀው ኃይል ደግሞ ለመከላከያ ሰራዊት መረጃ አቀብላችኋል በማለት ጉዳት እያደረሰብን ነው ይላሉ፡፡

በሳዩ ወረዳ 2 ቀበሌዎች 80 የሚደርሱ ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው ወደ ጋምቤላና ነቀምት መሸሻቸን የአካባቢው ነዋሪ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። በተመሳሳይ ከሳዩ ወረዳ አጎራባች በሆነው ሐዋ ገላን በተባለ ወረዳም ስድስት ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸውን አንድ አካባውን ለቀው ወደ ነቀምት ከተማ መሄዳቸውን የነገሩኝ የአካባቢው ነዋሪ አስታውቀዋል፡፡

ሌላው በቀሌም ወለጋ አንፊሎ ወረዳ ነዋሪ የሆኑና በአካባቢው ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት ቡራዩ መኖር ከጀመሩ ሁለት ሳምንት እንደሆናቸው የነገሩኝ የአካባቢው ነዋሪ በሰላም ወጥቶ በሰላም መግባት አዳጋች ነው ብለዋል፡፡ በአንፊሎ አንድ ገጠር ቀበሌዎች ውስጥ አራት ሰዎች ከታጣቂዎች ጋር ግንኙነት አላቸው ተብሎው መገደላቸውን ተናግረዋል።

የኦሮሚያ ክልል ኮምዩንኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ በአካባቢው የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ሕግን የማስከበር ሥራ እያከናወኑ ነው ያሉ ሲሆን በመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች በህዝቡ ላይ የደረሰው ጉዳት ካለ ተጣርቶ ይፋ ይደረጋል ብለዋል፡፡ በዞኑ ያለውን የጸጥታ ችግር በአጭር ጊዜ ለመፍታት የፌደራል እና የክልል ጸጥታ ሐይሎች በጋራ እየሰሩ እነደሆነ ገልጸዋል፡፡በቄለም ወለጋ ዞን እና ስሩ ከሚገኙት የወረዳ ስራ ኃላፊዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያረኩት ጥረት የስልክ አገልግሎት ባለመኖሩ አልተሳካም። – ዶይቼ ቬለ


የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV