" /> ካናዳ በኮሮና ቫይረስ ስጋት ከጃፓኑ የኦሊምፒክ ውድድር እራሷን አገለለች | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

ካናዳ በኮሮና ቫይረስ ስጋት ከጃፓኑ የኦሊምፒክ ውድድር እራሷን አገለለች

ካናዳ በዚህ ዓመት ይካሄዳል ተብሎ ከሚጠበቀው የጃፓን ኦሊምፒክ ውድድር እራሷን አገለለች።በኦሎምፒክ ዋነኛ ተሳታፊ ከሚባሉት አገራት መካከል የሆነችው ካናዳ እራሷን በማግለሏ በውድድሩ መካሄድ ላይ ተጨማሪ ጥርጣሬ ጥሏል።ካናዳ ይህንን ውሳኔዋን ያሳወቀችው የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ለመጀመሪያ ጊዜ የኦሊምፒክ ውድድሩ ለሌላ ጊዜ ሊተላለፍ ይችላል በማለት ከተናገሩ በኋላ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአውስትራሊያ የኦሊምፒክ ቡድን እንዳለው አሁን ባለው ሁኔታ ውድድሩ በተያዘለት ጊዜ እንደማይካሄድ “ግልጽ እየሆነ በመምጣቱ” ተሳታፊ አትሌቶች ለቀጣዩ ዓመት እንዲዘጋጁ ተነግሯቸዋል።ጃፓን ለማስተናገድ ለዓመታት ስትዘጋጅለት የነበረው የ2020ው ኦሊምፒክ ውድድር ከአራት ወራት በኋላ በሐምሌ ወር ላይ ነበር የሚካሄደው።
የካናዳ የኦሊምፒክና ፓራኦሊምፒክ ኮሚቴ ውሳኔውን በተመለከተ እንዳለው፤ ከውድድሩ ለመውጣት “አስቸጋሪ” ካለው ውሳኔ ላይ ከመድረሱ በፊት ከአትሌቶች፣ ከስፖርት ቡድኖችና ከካናዳ መንግሥት ባለስልጣናት ጋር መመካከሩን ገልጿል።ኮሚቴው ጨምሮም ለዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ ለዓለም አቀፉ የፓራኦሊምፒክ ኮሚቴና የዓለም የጤና ድርጅት የኦሊምፒክ ውድድሩ በአንድ ዓመት እንዲዘገይ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።
ምንጭ፡- ቢቢሲ

የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV