" /> የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር የተሳፋሪውን ቁጥር 50 በመቶ ቀንሶ አገልግሎት እየሰጠ ነው | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር የተሳፋሪውን ቁጥር 50 በመቶ ቀንሶ አገልግሎት እየሰጠ ነው

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት ከዛሬ ጀምሮ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር የተሳፋሪውን ቁጥር 50 በመቶ ቀንሶ አገልግሎት እየሰጠ ነው።የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ፥ እርምጃው የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር ያለ መሆኑን አስታውቀዋል።አያይዘውም ህብረተሰቡ የትራንስፖርት ጥግግት መጠንን በመቀነስ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር የድርሻውን እንዲወጣም ጠይቀዋል።


የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV