ሕዝቡ ገና ማህበራዊ ጥግግትን አልለወጠም- በሰዎች መካከል ከፍተኛ መተፋፈግ አለ- ቁጣው እሰኪያልፍ እንሸሸግ – ዶክተር ስለሺ በቀለ ( ሚኒስትር)

Imageዛሬ ወደ መገናኛ ብቅ ብዬ ነበር፡፡ COVID-19 በሽታን እንዴት እየተከላከልን ወይም ከችግሩ እንዴት እየተጠነቀቅን እንደሆነ ለማየት፡፡

የሚታየው ጥሩ አይደለም፡፡ ሕዝቡ ገና ማህበራዊ ጥግግትን አልለወጠም፡፡ በሰዎች መካከል ከፍተኛ መተፋፈግ አለ፡፡

በየአንዳንዱ ሰው መሀከል ያለው ርቀት 50ሳ.ሜ. አይሆንም እንኳንስ 2ሜ: ሁለቱን ፎቶዎች ዛሬ 11 ሰአት ላይ ያነሳሁትን ለማሳያ ብታዩ ብዙ ማለት ትችላላችሁ፡፡ አስቡት ዛሬ እሁድ ነው፡፡ ብዙ ሰው ይንቀሳቀሳል ተብሎ አይጠበቅም፡፡

በርግጥ የትራንስፖርትእጥረቱ፤ ተሯሩጦ ኑሮን ማሸነፉ ቢኖርም፤ ይህ ቀሳፊ ችግር እሰኪያልፍ እባካችሁ እንጠንቀቅ፡፡አንዴ ከቁጥጥር ከወጣ እጅግ በጣም አሰከፊ ችግር አገራችንና፤ እያንዳንዳችንን የማንወጣው አዘቅት ውስጥ ይከተናል፡፡ 

ችግሩን በፅናት እንቋቋም፡፡ ቁጣው እሰኪያልፍ እንሸሸግ፡፡ እሰኪያልፍ ያለፋል እንዲሉ፡፡ – ዶክተር ስለሺ በቀለ የውሐ መስኖና ኃይል ሚኒስትር 

Image