" /> በጣሊያን የመቀበሪያ ቦታ ሞላ : “ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ያጋጠመን ከፍተኛ ቀውስ ነው“ – የጣሊያን ጠ/ሚ ጆሴፔ ኮንቴ | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

በጣሊያን የመቀበሪያ ቦታ ሞላ : “ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ያጋጠመን ከፍተኛ ቀውስ ነው“ – የጣሊያን ጠ/ሚ ጆሴፔ ኮንቴ

በጣሊያን ቤርጋሞ የተሰኘው የመቀበሪያ ቦታ ሞላ
በጣሊያን ቤርጋሞ የተሰኘው የመቀበሪያ ቦታ በመሙላቱ በኮረናቫይረስ ምክኒያት ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎችን አስክሬን የጫኑ የጣሊያን የጦር ሰራዊት የጭነት መኪኖች ፌሬራ በተሰኘው የመቀበሪያ ቦታ ሲደርሱ።
ጣሊያን በዛሬው ዕለት ብቻ 793 ሰዎችን በሞት በመነጠቋ የሟቾች ቁጥር ወደ 4,825 ደርሷል፡፡ ከዚህ ጭንቅ ውስጥ ለመውጣት በጣሊያን ከተላለፈው ውሳኔ አንዱ እጅግ በጣም አስፈላጊ ከሆኑ ቦታዎች በስተቀር እስከ ሚያዚያ 3 ሁሉም ነገር እንዲዘጋ ማድረግ ነው፡፡

የ ኮረናቫይረስ ኮረናቫይረስ ወረርሽኝ በጣሊያን

ይህ ፎቶ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክኒያት እንቅስቃሴዋን በገታችው ጣሊያን በደቡብ ምስራቋ ሚላን አቅራቢያ ሎምባርዲ በሚገኘው ክሪሚና ሆስፒታል ውስጥ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ ያጠለቁ ሁለት ነርሶች የሥራ ሰዓታቸውን አንዳቸው ለሌላኛቸው በሚያስረክቡበት ጊዜ እርስ በእርሳቸው ሲፅናኑ የሚያሳይ ነው፡፡ የሕክምና ባለሞያዎቹ ለሳምንታት ባሳዩት ትግል ዓለም በጀግንነት እያወደሳቸው ቢሆንም፤ በጣሊያን የሚገኙት የጤና ባለሞያዎቹ ግን ከኮረናቫይረስ ወረርሽኝ ጋር በሚያደርጉት የጦርንት ግብግብ እጅግ በጣም ተዳክመዋል፡፡
ጣሊያን በዛሬው ዕለት ብቻ 793 ሰዎችን በሞት በመነጠቋ የሟቾች ቁጥር ወደ 4,825 ደርሷል፡፡ ከዚህ ጭንቅ ውስጥ ለመውጣት በጣሊያን ከተላለፈው ውሳኔ አንዱ እጅግ በጣም አስፈላጊ ከሆኑ ቦታዎች በስተቀር እስከ ሚያዚያ 3 ሁሉም ነገር እንዲዘጋ ማድረግ ነው፡፡
በአሁኑ ሰዓት ከሱፐር ማርኬት፣ከመድሃኒት ቤቶች፣ከፖስታ ቤትና የባንክ አገልግሎት በተጨማሪም አንዳንድ ሕዝባዊ አገልግሎት ከሚሰጡ ተቋማትና የመጓጓዣ አገልግሎት በስተቀር ሁሉም ነገር እስከ ሚያዚያ 3 እንዲዘጋ ተወስኗል፡፡
የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆሴፔ ኮንቴ “ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ያጋጠመን ከፍተኛ ቀውስ ነው” ሲሉ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ በቪዲዮ ባስተላለፉት መልዕክት ተናግረዋል።፡፡ከሐሙስ ዕለት ጀምሮ በዚህ በከፍተኛ ደረጃ ተላላፊ በሆነው የኮረናቫይረስ ወረርሽኝ በመጠቃት ጣሊያን ከቻይና ቀጥሎ ሁለተኛዋ አገር ናት፡፡
የማቾች ቁጥር ከ793 በመመዝገቡና አጠቃላይ ቁጥሩ ወደ 4,825 በማሻቀቡ ቫይረሱ በአገሪቱ መኖሩ ከተረጋገጠ ከአንድ ወር ጀምሮ ይህን ያልህ ሰው በአንድ ቀን ሲሞት የመጀመሪያው ትልቁ ቁጥር ነው፡፡
ሎምባርዲ የተባለችው በጣሊያን ሰሜን ግዛት ሚላን አቅራቢያ የምትገኘው ከተማ በከፍተኛ ሁኔታ ለኮረና ቫይረስ የተጋለጡ ሰዎች ያሉባት ከተማ ሆናለች፡፡ በአሁኑ ሰዓትም፤ 3095 ሰዎች ሕይወታቸውን ተነጥቀዋል፡፡ 25 ሺሕ ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡
በዓለም የጤና ድርጅት የዛሬ መረጃ መሰረት በመላው ዓለም 11,201 ሰዎች ሕይወታቸውን በኮረናቫይረስ ተነጥቀዋል፡፡ 267,013 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡
(AFP/ Reuters)

የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV