" /> ሁለት ተጨማሪ የኮሮና ቫይረስ ታማሚ ኢትዮጵያውያን መገኘታቸው ታወቀ | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

ሁለት ተጨማሪ የኮሮና ቫይረስ ታማሚ ኢትዮጵያውያን መገኘታቸው ታወቀ

ቀድሞ ከነበረው 9 ሰዎች ተጨማሪ 2 ከተያዙት ሰዎች አንደኛው የ28 ዓመት ኢትዮጵያዊ ሲሆን ቫይረሱ ከተዘማተባቸው ቤልጀም እና ኔዘርላንድስ ተጉዘው የነበሩ እና መጋቢት 5፣ 2012 ከቤልጀም ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱ ናቸው።2ኛው ደግሞ የ34 ዓመት ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ ከዱባይ ወደ ኢትዮጵያ የገቡት መጋቢት 10 ሲሆን፤ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በሚደረገው ምርመራ ምልክቱ ታይቶባቸው ለይቶ በማቆያ ተቀምጠው በላብራቷሪ ናሙና ምርመራ የተረጋገጠ ነው።

Image


የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV