ለጋራ ጥቅማችን ብሎ ለራሱ ከሚጠቀምብን ያድነን !!!


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ለጋራ ጥቅማችን ብሎ ለራሱ ከሚጠቀምብን ያድነን፡፡ ከሃዲዎች የዕጣ-ፈንታቸዉን ያገኛሉ::

የሳንቲሙ ገፅ ምን ዓይነት ነው? ዘውድ? ጎፈር? ወይም በሠያፍ የቆመ? መፈተሽ አለበት፡፡ተነስ ሲሉት የሚነሳ፣ ተኛ ሲሉት የሚተኛ … ዞሮ ዞሮ ወዶ-ገባ ያሉትን መፈፀም ግዴታው ነው፡፡ ወዶ-ገባ ዝርያው ብዙ ነው፡፡ የፖለቲካ ወዶ-ገባ አለ፡፡ ፖለቲካው ምንም ይሁን ምንም ለጥቅሜ እገባበታለሁ ይላል፡፡ የኢኮኖሚ ወዶ-ገባ አለ፡፡ ኢኮኖሚው ምንም ይሁን ምን ሆዴን እሞላበታለሁ ይላል፡፡ የማህበራዊ ወዶ-ገባ አለ፡፡ ከማናቸውም ማህበራዊ ቀውስ እኔ ጥቅሜን ካካበትኩ ያሉኝን አደርጋለሁ ባይ ነው፡፡ ብልህ ሰው የውሾቹን ዓይነት ዕጣ-ፈንታ ያስተውላል፡፡ አበሻ፤ አብዶም ሠግዶም ውሉን አይስትም የሚል አባባል አለው፡፡ ይሄንንም ልብ-ልንበል፤ የህግ-ወዶ-ገባም አለ፡፡ በፍትሕ ሽፋን ጥቅሙን የማያጋብስ፡፡

አገርን የሚያጠፋ ማንኛውም ጥፋት ጥፋት ነው፡፡ ሚሥማርም አቀበልን ድንጋይ ያው ነው፡፡ በወገናዊነት ላንድ ቡድን መጠቀሚያ አመቻቸንም፣ በሙስና ውስጥ ተዘፈቅንም፤ ዞሮ ዞሮ አገርና ህዝብ በድለናል፡፡ እገሌ አድርግ ብሎኝ ነው እንጂ እኔ በራሴ አላደርገውም ነበር ማለት የኋላ ኋላ ከተጠያቂነት አያድንም፡፡ በሥርዓቱም ማሳሰብ በግልና በቡድን ከሠራነውና አንዱን የእናት ልጅ፣ አንዱን የእንጀራ ልጅ አድርገን ካጠፋነው ጥፋት ተጠያቂነት አያድንም፡፡ ሰው ሰውን መበዝበዙ ነው ሀቁ፡፡ ፊት ለፊቱም ግልባጩም ያው ነው እንደ ማለት ነው፡፡ስለዚህ ሥርዓት ሰበብ አይሆንም፡፡ ዕውነቱ ሰው ሰውን መበዝበዙ ነው፡፡ ሊበራል፣ ኒዮ ሊበራል፣ አብዮታዊ፣ ኮሙኒስታዊ፣ ፋሽስታዊ፣ ቦናፓርቲዝማዊ፣ ልማታዊ፣ ሉአላዊ፣ ፀረ-ሽብራዊ፣ ዲሞክራሲያዊ፣ ኢጋዳዊ፣ … ሁሉም የሰውና ሰው ተቃርኖና ፍጭት መልኮች ናቸው፡፡ ዋናው ከህዝብና ከሀገር ጥቅም አኳያ ምን ይመስላሉ ተብሎ መመርመር ያለባቸው ናቸው፡፡ የሰውና ሰው ግንኙነት የጨቋኝና ተጨቋኝ፣ የወገናዊና ኢወገናዊ፣ የፍትሐዊና ኢፍትሐዊ፣ ወይስ ቡድናዊና ኢቡድናዊ? ምን ይመስላል፡፡ የሳንቲሙ ገፅ ምን ዓይነት ነው? ዘውድ? ጎፈር? ወይም በሠያፍ የቆመ? መፈተሽ አለበት፡፡

አንዱ ለአመራሩ ሚሥጥር ቅርብ በመሆኑ አስቀድሞ ኢንፎርሜሽን ያገኛል፡፡ ቤቱን ከውርስ ያድናል፡፡ ሌላው ለኢንፎርሜሽኑ እሩቅ ነውና ላዩ ላይ ይታወጅበታል፡፡ ለብዙሃኑ ጥቅም ሲባል ጥቂቶቹ ቢጎዱም ምንም አይደለም የሚለውም አስተሳሰብ መመርመር ይኖርበታል፡፡ የአብዮቱ ጦስ ይሁን የካፒታሊዝም ጦስ ባልለየበት አገር አዋጆችና መመሪያዎች ሲከለሱ ማየት ቢያንስ ያስገርማል፡፡ አቀንቃኙ እና ተቃራኙ በቀላሉ አይለዩም፡፡ ከሥልጣን ይባረራሉ፡፡ ተባራሪዎቹ ያወጡት ህግና መመሪያ ምን እንደሚሆን ዕጣ-ፈንታው አይታወቅም፡፡ ከሁሉም ይሰውረን! ህዝብ ብቻ ግራ እንደተጋባ ይቀጥላል፡፡ሰው ይጫኑብህ ግንድ? ቢሉት፤ ግንድ ከተጫነኝ ሰው ያነሳልኛል፣ ሰው ከተጫነኝ ማን ያነሳልኛል፤ አለ የሚባለው ግራ-ገብ ዘመንን የሚያመላክተን ነው፡፡ ከዚህም ይሰውረን! ከሚጫነን ይገላግለን፡፡ ከወዶ-ገባነት ይቅር ይበለን!!

ምንሊክ ሳልሳዊ