“ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ በኤርትራ ፓስፖርት ይጓዝ ነበር- ስለዚህ እኔም በአሜሪካ ፓስፖርት በቀጣዩ ምርጫ ብወዳደር ችግር የለውም:: -ጃዋር መሃመድ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


“ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ በኤርትራ ፓስፖርት ይጓዝ ነበር ስለዚህ እኔም በአሜሪካ ፓስፖርት በቀጣዩ ምርጫ ብወዳደር ችግር የለውም:: ጃዋር መሃመድ 

ጃዋር “ዶ/ር ብርሃኑ የኢትዮጵያ ዜግነት የለውም። ስለዚህ ሁለታችንም በቀጣዩ ምርጫ ብንሳተፍ ችግር የለውም” እያለ ነው። ከብርሃኑ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ዜግነት የሌላቸውን የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና አባላትን በመዘርዘር ቢተባበረን መልካም ነው። ምክንያቱም ለህግ ተገዢ ያልሆኑትን በሙሉ ጠራርጎ ለማስወጣት ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል።

Image may contain: 1 person, text

***************** *** **************************
እውነቱን ለመናገር ከዜግነት ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ሰዎች እያነሱት ያለውን መናኛ አጀንዳ ብዙም ልገባበት አልፈለግኩም ነበር፤ ኾኖም አሁን በግድ ወደ አጀንዳው እያስገቡን ነው፡፡ እንደሚታወቀው ሁሉም በሚያስብል ደረጃ በውጪ ሀገራት የነበሩ ፖለቲከኞች፣ አክቲቪስቶችና ጋዜጠኞች የውጪ ሀገር ፖስፖርት ተጠቃሚዎች ነበሩ፡፡ ብዙዎቹ እነዚህ በውጪ ሀገራት የነበሩ ሰዎች ዛሬ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችን እየመሩና የጀርባ ታሪክና ዜግነትን ጭምር ማጣራትና መፈተሸን የሚጠይቁ ሚስጥራዊና ብሔራዊ ጉዳዮች ላይ ጭምር ውሳኔ የሚሰጡ ሰዎች ኾነዋል፡፡ የእነዚህን ሰዎችና የሥራ ድርሻቸውንም መጥቀስ ይቻላል፡፡
አስገራሚው ነገር ግን ከእነዚህ ሁሉ ሰዎች ተለይቶ የእኔ ብቻ የዜግነት ጉዳይ አጀንዳ እንዲኾን እየተደረገ ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል፡- የተጥቅ ትግል እንቅስቃሴ ሲመራ የነበረው ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ከዚህ ቀድም ባወጣው ዘገባ መሠረት (የተያያዘውን ምስል ይመልከቱ) የኤርትራ ፓስፖርት ነበር የነበረው፡፡ ይኼን መረጃ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ሰዎች በደንብ ያውቁታል፡፡ የሌሎችም በርካታ ከውጪ ተመላሽ ሰዎች የዜግነት ኹኔታ በምርጫ ቦርድ አመራር ሰዎች በደንብ ይታወቃል፡፡ (የብርሃኑ ነጋን እዚህ የጠቀስኩት ጉዳዩ በይፋ ጋዜጣ ላይም የታተመ ስለኾነ ነው) አስገራሚው ነገር የእኔ ዜግነት ላይ ብቻ ነጥለው ማትኮራቸው ነው፡፡ ለመኾኑ ፕሮፌሰር ብርሃኑንና ሌሎችንም ልክ እንደእኔ ዜግነታቸውን እንዲያረጋግጡ ጠይቀዋል? የእኔ ላይ እንዳደረጉት የብርሃኑን የዜግነት ጉዳይ ወደ ሚዲያ በማውጣት አጀንዳ አድርገውታል? አላደረጉም!
እኔን በተመለከት አንድም ቀን ቢኾን የአሜሪካ ዜግነት መውሰዴን ደብቄ አላውቅም፡፡ ለምርጫ እንደምወዳደር ከወሰንኹ በኋላ ግን የአሜሪካን ዜግነቴን መተው እንደምፈልግ በይፋ ገልጫለኹ፡፡ ለዚህም አስፈላጊውን ሂደት አከናውኛለኹ፡፡ ለአሜሪካ ኤምባሲ ፓስፖርቴን መልሻላኹ፣ የአሜሪካን ዜግነት ማጣቴንም የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት ተቀብያለሁ፡፡ በቀጣይነትም ይኼን ማስረጃና ሌሎች የሚጠየቁ ሰነዶችን በማሟላት ለሚመለከተው የኢትዮጵያ መንግሥት መሥሪያ ቤት አስገብቻለሁ፡፡ ይኼንን ያከናወንኩትንም ሂደት ፓርቲዬ ኦ.ፌ.ኮ ለኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ አሳውቋል፡፡ ይኼ ሁሉ ተከናውኖም የምርጫ ቦርድ ሰዎች ጉዳዩን ከማንሳት አልታቀቡም፡፡ ለምን ይኾን? ብዙዎች እንደሚጠረጥሩት ይኼን ሰበብ አድርገው በምርጫው እንዳልሳተፍ ሊያቅቡኝ ይፈልጋሉ፡፡ ምንአልባም እንደዛ አስበው ሊኾን ይችላል፡፡
1. መጀመሪያ በዚህ ቁርጡ ባልለየለት የፖለቲካ ኹኔታ የአሜሪካ ዜግነቴን በራሴ የምተው አልመሰላቸውም ነበር፡፡ ላጭበረብር እንዳሰብኩ ገምተውም ነበር፡፡ ምንም አይደል፤ ለዚህ አጉል ጥርጣሬያቸው ይቅር ብያቸዋለሁ፡፡ ለሕዝባችን መሻት ስንል እንኳን ፓስፖርታችንን አስፈላጊ ከኾነም ሕይወታችንን ለመስጠት ቁርጠኛና ዝግጁ እንደኾንን አልተረዱም፡፡
2. ዜግነት የመመለስ ሂደቱን እንደጀመርኩ ሲረዱ ደግሞ፣ ዜግነት የመመለሱ ሂደት ረዝሞ ምርጫው ሊያመልጠኝ እንደሚችል ተስፋ አደረጉ፡፡ ነገር ግን ሂደቱ ከገመቱት ውጪ በፍጥነት ተጠናቀቀና የአሜሪካን ዜግነት ማጣቴን የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት ተቀበልኩ፡፡
3. አሁን ከእኔ የሚጠበቁ ሕጋዊ ሂደቶችን ሁሉ ፈጽሜም እንኳ የምርጫ ቦርድ ሰዎች የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ላይ ጫና በመፍጠር ሂደቱን ለማወሳሰብ እየሞከሩ ነው፡፡ ኾኖም ይኼን ለማድረግ ምንም የሕግ ድጋፍ የላቸውም፡፡ በእኔ በኩል የሚጠበቁ ሦስት ሂደቶችን በአግባቡ ፈጽሚያለኹ፡፡ የዜግነት ሰነድ መልሻለኹ፣ የቀድሞ ዜግነቴን ጥያለኹ፣ ማመልከቻዬንና ሰነዶቼን ለሚመለከተው የመንግሥት ቢሮ አስገብቻለሁ፡፡
ጉዳዩ ለሚያሳስባቸው ወገኖች የምለው ነገር፡- በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የምናደርገው ነጻ፣ ገለልተኛና ፉክክር የተመላበት ምርጫ ላይ ሙሉ ትኩረታችንን እንድናደርግ ነው፡፡ ይኼንን ታሪካዊ አጋጣሚ በአግባቡ እንዳንጠቀም ከሚያደርጉ መናኛ አጀንዳዎች ራሳችንን እናርቅ፡፡ በእኛ በኩል የጨዋታውን ሕግ እናውቀዋለን፣ ለሕጉም ተገዢዎች እንኾናለን፡፡ ሕጉን በምንም መልኩ የመጣስ ፍላጎት የለንም፡፡ በምርጫው ሰላማዊና ሕጋዊ ኾነን በሙሉ ልባቸውን ነው የምንሳተፈው፡፡ በዚህ ሂደት ከማንም አካል ውለት አንጠይቅም፤ ከማንም በተለየ መድልኦ እንዲደረግብንም አንሻም፡፡ ብዙ የለፋነውና መስዋእትነትም የከፈልነው ለዚህ ታሪካዊ አጋጣሚ ለመብቃት ነው፡፡ ሂደቱ ፍሬ እንዲያፈራም በቃላችን ታምነን እንቆያለን፡፡
I really did not want to dwell on this silly issue of citizenship that the NEBE is pushing but it seems they are determined to drag us into it. It is public knowledge that most if not all of exiled political leaders, activists and journalists were using foreign passport. Many of these formerly exiled personalities today lead political parties or work for the government handling sensitive national security matters that require strict background check including citizenship status. We can name names and positions. However it’s only my citizenship that has become agenda. For instance Brehanu Nega who back then led rebel movement and who now chairs a registered political party had Eritrean citizenship as reported by the New York Times ( see screenshot). This fact was intimately known to the NEBE leadership. There are several other political personalities whose citizenship status is well known by the NEBE leadership. ( I mentioned Brehanu just because his issues is publicly available). Yet they are making fuss only about my case !! Have they asked Brehanu and others to provide evidence of citizenship? Did they take his issue to the public by making rounds on media? No they did not !!
I never hide the fact that I obtained American citizenship while in exile. Once I decided to pursue office, I made it clear my intention to renounce my American citizenship. I took necessary steps immediately. I returned my American passport to the US embassy. Subsequently I received Certificate of Loss of Nationality. I submitted these and other required documents to the relevant agency of the Ethiopian government. And my party informed NEBE. Yet they continue to push this agenda publicly. Why? Many suspect they are trying to find pretext to exclude me from the election. May be.
1. Initially they hoped I won’t dare abandon my US citizenship at this time of political uncertainty. They thought I was trying to deceive. Well I forgive them. They don’t know how determined and prepared we are to give up not just passport but even our lives, if it comes to that, for the cause of our people.
2. Once they learned I had initiated the process, they hoped the process of renouncing my citizenship will take long and make me miss the election deadlines. Yet the process did not take as long as they hoped. It was completed much faster.
3. Now I have fulfilled all that is legally expected of me, they hope to pressure the Ethiopian authorities to complicate things. However, they have no legal ground whatsoever. I have fulfilled all the three requirements for readmission i.e. return to domicile, renounce foreign citizenship and submit application informing the authorities. All three are done.
My advice to all concerned is; let’s focus on paving the way to hold our first free, fair and competitive election. Let’s not dwell on silly issues that will distract us from utilizing this historic opportunity. On our side we know rules of the game, we will abide by them. We won’t bend let alone break it. We will contest this election peacefully, legally and passionately. We don’t ask for any special favor nor do we allow to be discriminated against. After all we worked hard and sacrificed a lot to bring about this historic opportunity. We remain committed to see it succeed. – Jawar Mohammed