" /> የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ሥርጭትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ጸደቀ | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ሥርጭትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ጸደቀ

EBC : የፀረ-ጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ሥርጭትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የቀረበው ረቂቅ አዋጅ በአብላጫ ድምፅ ጸደቀ
ረቂቅ አዋጁ የጸደቀው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን በዛሬው ዕለት ባሄደው 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባው ነው፡፡

ምክር ቤቱ የፀረ-ጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ሥርጭትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የቀረበውን ረቂቅ አዋጁን በ23 ተቃውሞ ፣ በሁለት ድምፀ ተአቅቦ በአብላጭ ድምፅ አዋጅ ቁጥር 1185/2012 እንዲሆን አጽድቆታል።

በምክር ቤቱ በተደረገ ውይይት ላይ በአሁኑ ወቅት በኅብረተሰቡ መካከል ያሉ መልካም እሴቶች በጥላቻ ንግግሮች እና በሐሰተኛ መረጃ ስርጭት ምክንያት እየተሸረሸሩ እና ለአገርም ስጋት የደቀኑ መሆናቸው ተጠቅሷል።

በመሆኑም አዋጁ መሰልና ሌሎች ተያያዥ ችግሮችን ለመከላከል ዓይነተኛ ሚና እንደሚጫወት ምክር ቤቱ አመልክቷል፡፡

 


የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV