የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ በገንዘብ የሚደግፋቸውን አምስት ፕሮጀክቶች ይፋ አደረገ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


No photo description available.EBC : የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ለመጨረሻ ዙር ከቀረቡ 22 ፕሮጀክቶች መካከል መመዘኛውን ያሟሉትንና በገንዘብ የሚደግፋቸውን አምስት ፕሮጀክቶች ይፋ አደርጓል።የትረስት ፈንዱ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ወ/ሮ ሃና አጥናፉ ፕሮጀክቶቹ የተመረጡት ለትረስት ፈንዱ ገንዘብ ያዋጡ የዳያስፖራ አባላትን ፍላጎትና የፕሮጀክት አማካሪዎችን አስተያየት መሰረት በማድረግ ነው ብለዋል፡፡

ፕሮጀክቶቹ በውሃ፣ ትምህርትና በጤና ላይ የሚያተኩሩ መሆናቸውን ገልጸው፣ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቁና በአጠቃላይ 50 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ መሆናቸውንም ኃላፊዋ ገልፀዋል።ከፕሮጀክት ባለቤቶቹ ጋር የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም በቅርቡ ወደ ስራ እንደሚገባ የገለጹት ወ/ሮ ሃና፣ የፕሮጀክቶቹ አፈጻጸም እየታየ ደረጃ በደረጃ የገንዘብ ድጋፉ የሚለቀቅ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ቀሪዎቹ 17 ፕሮጀክቶችም በአማካሪ ምክር ቤቱ የታየባቸውን ጉድለት ሲያሟሉ ከፈንዱ ጋር የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ወደ ስራ እንደሚገቡ አረጋግጠዋል።በእስካሁኑ ሂደት ትረስት ፈንዱ ከ25 ሺ በላይ ከሚሆኑ ለጋሾች ወደ ስድስት ሚሊዮን የሚጠጋ የአሜሪካን ዶላር ማሰባሰብ መቻሉ ታውቋል።

ምንጭ፦ ኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲ