የምርጫ ቦርድ አካሔድ ማንን ለመጥቀም ይሆን ?


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የምርጫ ቦርድ አካሔድ ማንን ለመጥቀም ይሆን ?
 
ሕግ ይከበራል ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው። ምርጫ ቦርድ ከቀኑ አይዘልም ያለው የግንቦቱ ምርጫ ለነሐሴ ተላልፏል ተብለን ነበር ። አሁን ደግሞ የነሐሴው ምርጫ ወደ ጥቅምትና ሕዳር 2013 ሊዘል ይችላል። ይህቺ አካሔድ ማንን ለመጥቀም ይሆን ???
 
ሐገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የሚካሔድበት ቀን አልተቆረጠለትም የሚል አለማማጅ ፕሮፓጋንዳ ከምርጫ ቦርድ በኩል ተለቃለች።ሕግ እየጣሱ በግልጽ የምርጫ ቅስቀሳ ያደረጉ ፓርቲዎችና ግለሰቦች ከሕግ አግባብ መጠየቅ ሲኖርበት ገና ምርመራ አለመጀመሩ የቦርዱን ንዝሕላልነት ያሳያል። የምርጫውን ክራይቴሪያ ያላሟሉ ግለሰቦች ዶክመንታቸውን አስጨርሰው እስከሚመጡ ምርጫ የለም እየተባለን መሆኑን ስንቶቻችን ተገንዝበናል ???
 
የሐገሪቱ ሕገ መንግስት በሚያዘው መሰረት ምርጫው መፈጸም ሲገባው በቀነ ቀጠሮ መንዘላዘል ከሕግ አንፃር የሚያስነሳው ውዝግብ ማን ሊፈታው ይችላል የሚለው እንደተጠበቀ ሆኖ ምርጫ ቦርዱ ለተወሰኑ አካላት ጥቅም ሲል በውይይት ሽፋን የሕዝብን መብትና ሕግን እየደፈጠጠ ነው። የምርጫ ቦርድ አካሔድ ማንን ለመጥቀም ይሆን ? ልብ ያለው ልብ ይበል !!! #MinilikSalsawi