" /> መንግስት መለቀቃቸውን ያስታወቀው ሃያ አንድ ተማሪዎች ደምቢዶሎ ዩንቨርስቲ ተመልሰዋል ተባለ | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

መንግስት መለቀቃቸውን ያስታወቀው ሃያ አንድ ተማሪዎች ደምቢዶሎ ዩንቨርስቲ ተመልሰዋል ተባለ

DW : ከደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲሄዱ ከታገቱ በኋላ መንግስት መለቀቃቸውን ያስታወቀው ሃያ አንድ ተማሪዎች ወደ ደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ መመለሳቸውን የኦሮሚያ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ከዶይቸ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ተናገሩ። ተማሪዎቹ ከእገታ ከተለቀቁ በኋላ ከወላጆቻቸው ጋር ያልተገናኙት በአካባቢው የስልክ ግንኙነት አገልግሎት ባለመኖሩ የተነሳ መሆኑንም አቶ ጌታቸው ዛሬ ተናግረዋል።

የታገቱ ቀሪ ስድስት ተማሪዎችን ለማስለቀቅም ጥረት እየተደረገ መሆኑንም አመልክተዋል። ከኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ከአቶ ጌታቸው ባልቻ ጋር የስልክ ቃለ-ምልልሱን ያደረገው ታምራት ዲንሳ ነው። ተማሪዎቹ ደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ መኖራቸውን ለማጣራት ወደ ዩኒቨርስቲው ስልክ ብንደውልም ባለመስራቱ ሳይሳካ ቀርቷል።

 


የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV