" /> ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ግቢውን የለቀቁ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ አሳሰበ | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ግቢውን የለቀቁ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ አሳሰበ

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ግቢውን የለቀቁ ተማሪዎች በአስቸኳይ እንዲመለሱ አሳሰበ

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ፦ «በአገሪቱ የተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተፈጠሩ አለመረጋጋቶች» በራሳቸው ምክንያት ግቢዎችን ለቀዋል ያላቸው ተማሪዎች «በአስቸኳይ ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመልሰው ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ» ሲል አሳሰበ። የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ሰሞኑን በጉዳዩ ላይ በጥልቀትና በትኩረት ከተወያየ በኋላ ተማሪዎቹ ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ መወሰኑንም ይፋ አድርጓል።

ውሳኔው ከዚህ ቀደም የተቀጡ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ካልገቡ አንማርም በማለታቸው ምክንያት ታኅሣሥ 8 ቀን፣ 2012 ዓ.ም ከዩኒቨርሲቲው ተባርረው የነበሩት የባህር ዳር የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተማሪዎችንም እንደሚያካትት የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሙኒኬሽን ምክትል ፕረዚደንት ዶ/ር ዘውዱ እምሩ አመልክተዋል።

ተማሪዎቹ ከጥር 5 እስከ ጥር 7 ቀን፣ 2012 ዓ.ም «እስከ 11፡30 ድረስ» ተጠቃልለው እንዲገቡ ዩኒቨርሲቲው ሴኔት መወሰኑን ዩኒቨርሲቲው በፌስቡክ ገፁ ይፋ ዐስታውቋል። በተባለው ጊዜ «በትምህርት ገበታ ላይ መገኘት ያልቻለ ተማሪ ቢኖር ከዩኒቨርሲቲው እንደተሰናበ እንደሚቆጠር» የዩኒቨርሲቲው ሴኔት «በጥብቅ» ማሳወቁም ተገልጧል።

ዘገባው የDW ነው።


የመረጃ ቲቪ አባል ይሁኑ - JOIN US