የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል መካኖችን ለመጀመሪያ ጊዜ ልጅ አስታቀፈ።


ኢትዮጵያን ካጋጠሟት እጅግ ውስብስብ ችግሮች ለማዳን የተለያዩ ጠቃሚ ሃሳቦችን እና ገንቢ ትችቶችን የሚያቀርቡ ነፃ ሚዲያዎች ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ይታወቃል። ስለዚህም ኢትዮ360፣ መረጃ ቲቪ፣ አዲስ ድምጽ፣ ምንሊክ ቲቪ እና ሌሎችም የኢትዮጵያዊነት አጀንዳ የሚያራምዱ ሚዲያዎች በመተባበር ፕሮግራሞቻቸውን በሳተላይት ቲቪ ለኢትዮጵያ ህዝብ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ሚዲያዎች የፈጠሩት ማህበር የሳተላይት ወጪውን መሸፈን እንዲያስችለው ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ ከፍተናል → እዚህ ሊንክ ላይ ይጫኑ። ለትብብርዎ እናመሰግናለን።

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ መካኖችን ለመጀመሪያ ጊዜ ልጅ አስታቀፈ።

በመካንነት ሕክምና ማእከል ህክምናቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ጥንዶች በ`intro vitro fertilization’ ህክምና ልጅ ማግኘት ችለዋል፡፡ ጥንዶቹ ለሰባት ዓመታት በጋብቻ ሲኖሩ ልጅ ማፍራት አልቻሉም ነበር፡፡ እነዚህ ባልና ሚስት የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ማእከሉ ባለፈው ሚያዚያ 2011 ተመርቆ ከተከፈተ በኃላ የመጀመሪዎቹ በIVF ሕክምና ልጃቸውን የታቀፉ ወላጆች ሆነዋል፡፡

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ለመላው ባለሙያዎቹና ተገልጋዮቹ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፏል። በIVF ሕክምና የሚወልዱ ቁጥራቸው 70 የሚደርሱ ነፍሰጡር እናቶችም በቀጣይ ወራቶች ልጃቸውን ለማቀፍ ይበቃሉ፡፡ በኢትዮጵያ ያለመውለድ ችግር/ መሃንነት/ ስርጭት ከፍተኛ መሆኑ ቢታመንም በተወሰነ መልኩ ምርመራዎችን ከማድረግ የዘለለ በበቂ ሁኔታ የህክምና መፍትሔ ለመስጠት የሚያስችል የተደራጀ የህክምና ተቋም አልነበረም፡፡

በመንግስት የጤና ተቋም የጳውሎስ የመጀመሪያው ነው ተብሏል፡፡ ከዚህ ቀደም ብዙ ጥንዶች ወደ ውጪ ሃገር ሄደው በከፍተኛ ወጪ ለመታከም ይገደዱ ነበር፤ በዚህም ሀገራችን ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሪ ይባክን ነበር፡፡ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በመጪው ሁለት ዓመታት በሀገር ውስጥ የማይገኙ ሌሎች የሕክምና አገልግሎቶችን ለመጀመር በሂደት ላይ ነው ተብሏል፡፡

Source : የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ