ከእገታው የተለቀቁት ተማሪዎች በመንግሥት እጅ ናቸው ማለት ምን ማለት ነው ???


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ከእገታው የተለቀቁት ተማሪዎች በመንግሥት እጅ ናቸው ማለት ምን ማለት ነው ??? … መንግስት ወዴት እያመራ ነው ???

የመንግስት ባለስልጣናት መቀባጠርና ማደናገር አሁንም ቀጥሏል። የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ እንዳለው የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደር እና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ ከእገታው የተለቀቁት ተማሪዎች አሁን በመንግሥት እጅ መሆናቸውን ተናግረዋል።

እገታውን የሚያጫውተው የመንግስት መዋቅር ነው ስንል ከምንም ተነስተን አይደለም። ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ሰው ንጉሱ ጥላሁን ጀምሮ የኦሮሚያና አማራ ክልል ባለስልጣናት ሳይናበቡ የሚናገሩት ነገር ሁሉ መንግስት በተማሪዎች እገታ ላይ የራሱ ሚና እንዳለው በቂ ምስክር ነው።

መንግስት ተማሪዎቹን ሆን ብሎ አጀንዳ ለመፍጠር አግቷል ወይንም አግቶ በወለጋ ለሚያካሂደው ጦርነት እንደ ሽፋን እየተጠቀመባቸው ነው።ከታች በምድርና ከላይ በአየር ኃይል ጦርነት በኦነግ ወታሮች ላይ የከፈተው መንግስት የሚፈልገው ግብ ላይ እስኪደርስ ተማሪዎቹን እንደ ካርድ እየተጠቀመባቸው አስመስሎበታል።

ከእገታ ተለቀቁ የተባሉ ተማሪዎችን ዛሬም እንዳላገኙ ቤተሰቦቻቸው እየተናገሩ ነው።ታጋቾቹ በመንግስት እጅ ከሆኑ ተሐድሶ ተሰጥቷቸው የሚለቀቁም ከሆነ መንግስት በሚዲያዎቹ በግልጽ መስመር ማሳወቅ ሲኖርበት የተማሪዎቹን ወላጆች በስጋት ማኖር ሕዝብን ከሚያስተዳድር አካል አይጠበቅም። #MinilikSalsawi

ከእገታው የተለቀቁት ተማሪዎች በመንግሥት እጅ ናቸው ማለት ምን ማለት ነው ??? … መንግስት ወዴት እያመራ ነው ???

#BringBackOurStudents #ReleaseThem #የታገቱትይለቀቁ