የተማሩ የኦሮሞ ምሁራን ማደናቆር ወይንስ መደንቆር? እና የዶክተር መረራ የቁመትልክ ስልጣን


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Image may contain: Mengistu Musie, smiling

Mengistu Musie

የተማሩ የኦሮሞ ምሁራንማደናቆር ወይንስ መደንቆር? እና የዶክተር መረራ የቁመትልክ ስልጣን
በመንግስቱ ሙሴ

ኢትዮጵያዊው ማነው? የሚል ጽሁፍ በ 1960 ወቹ መጀመሪያ ያቀረቡት የያኔ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዩኒቨርስቲ ተማሪ በየካቲት አብዮት ማግስት መጀመሪያ መኢሶን ኋላ ኦነግ ሆነው ዘመናቸውን ኖረዋል። ያነን መጣጥፍ ለተማሪው ያቀረቡት የያኔ ተማሪ ዘመን እድሜአቸውን ኢትዮጵያዊነት የተሰማቸው እንዳልሆኑ መገመት ከባድ አይደለም። የኔ የሁልግዜ ጥያቄ ይህ ነው። የኔ እና መሰል ዘመዶች አያት ቅድም አያቶች የሀገር ዳር ድንበር ሲደፈር ጭብጦ ይዘው ሲዘምቱ እና ሲቆስሉ ሢሞቱ እንደኖሩ ሲነገረኝ አድጌአለሁ። ባንዳነት ክህደት እና ሀገርን አሳልፎ መስጠት የተጸየፉት ዘመዶቸ በቁመቴ ልክ ስልጣን ሳይሉ እንዳለፉም አውቃለሁ። አያቴ ከሽሬ መልስ በመርዝጭስ ያጋጠማቸውን አይነስውርነት በጸጋ ተቀብለው እንዳለፉም ተደጋግሞ ተነግሮኛል። ለሀገር በተደረገው ሁሉ ዋጋ ከፈላ አይደለም የቁመት ያህል ስልጣን ለደከሞ ለቆሰሉበት መዳሊያ ሳያገኙ የበላይ ተከታይ ተብለው ያለፉ ዘመዶቸን ሳስታውስ ስለሀገር የከፈሉትን ዋጋ ጠያቂወች እንዳልነበሩ/ይከፈለን እንዳላሉ በይበልጥም ማንም ምንም ይበል እነርሱ ግን በሰሩት ስራ ከማንም ምርቃት ወይንም ሽልማት ሳይጠብቁ በኩራት እንዳለፉ የሚገባኝ አሁን ነው።
የአጭሯ ታሪክ መነሻየ የዶክተር መረራ በቁመታችን ልክ ስልጣን እና የብዙ የእርሳቸው መሰሎች ሁሉንም ጠቅለው ቢይዙ አሁንም ጭቁን ነን ከሚለው አስተሳሰብ ነጻ ሊሆኑ እንደማይችሉ ዘመን አስቆጣሪ አስተሳሰብ መሆኑን ነው። ከ 19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከቅርቡ ግዜ እንኳን ብንጀምር ከጎበና ዳጨ እስከ ኀብተጊወርጊስ ዲነግዴ፣ ጄኔራል ተፈሪ ባንቲ እስከ መንግስቱ ኃይለማሪያም የሀገሪቱ ጫፍ ስልጣን በማን እጅ ነበር አሁንስ ዛሬ በማን እጅ ነው ያለው? ብሎ የሚጠይቅ ልቦና እና አዙሮ ማየት የሚችል አንገት ሊኖር ባለመቻሉ የሁልግዜ ተገፍተናል አስተሳሰብ ዳር ዳርቻ አጥቷል። ሁልግዜ ተበደልሁ እና ሁልግዜ ይገባኛል ብቻ ሲሆን ዳር የለሽ ይሆንና በእውነት እየተበደለ ያለው ሕዝብ አምርሮ ከተነሳ መላሽ የሚያጣበት ሁኔታ እንዳይፈጠር ግን ያስፈልጋል።

ዶከት መረራ ሁልግዜ በቁመታችን ልክ ስልጣን ይገባናል ሲሉ ዘመናት ያለፈ ንግግራቸውን አዳምጣለሁ። ይህ አስተሳሰባቸው ከአንድ የተማረ ያውም ታሪክ እና ፖለቲካን ከልጅነት እስከውቀት የሰራበትን ሰው ሳስብ ሀገር በአዋቂወች እና ልምድ ባላቸው ሰወች ከእውቀት ይልቅ ዘርን መስፈርት ያደረገ ይሁን ብሎ ሲያላዝን መስማት ምን ያህል ተስፋ አስቆራጭ እንደሆነ መገመት ያስቸግራል። ለዚያውም ከዚህ ያለፈ ስልጣንን የመጠቅለል appetite በዘረኞች እና በዘመናቸው የሚከሰት ሕዝብን እና ሀገርን ወደ እድገት ሳይሆን ወደአመጽ እና መናቆር የሚመራ መሆኑን ከህወሓት አይተናል አሁንም እያየን ነው።

ሀገር የጋራ ብሎ ማሰብ። ለነጻነት እና በሰላም ተንቀሳቅሶ ለመስራት መታገል። ዘረኝነትን አስወግዶ ኢትዮጵያውያን የሆነ ሁሉ ባሻው እና በሚመቸው ኖሮ እና ሰርቶ በነጻነት እንዲንቀሳቀስ መፍቀድ ከሁሉም እና ከማነኛውም የበለጠ ለእድገት ይጠቅማል። ዘሬ ተበደለ ብሎ ማሰብ እና ሁሉም ለእኔ ዘር ብሎ መመኘት ዳር ድንበር የለውም መጨረሻውም ልክ እንደህወሓቷ የሚያምር አይደለም። ዘረኝነት በሽታ ነው እንደህወሓት እና ኦነግ መታመም።

መድሀኒትም የለውም እራሱ በልቶ እና ገዝግዞ ያው ፈጣሪውን የጨርሰዋል። ዶክተር መረራን ማየት በቂ ምሳሌ ይሰጣል። በብዙ ኢትዮጵያውያን የተከበሩት ሰው በቁመት ልክ በሚሉት አስተሳሰብ ስግብግብነት አገር ገዳይ ከሆኑት ከነጃዋር እና በቀለ ገርባ ጋር አንድ ሆነው ሲሰሩ ማየት; The tension between individual right and group discrimination targeted on the pretext of cultural equality and groups constitute one enduring paradox of Ethiopian society.

Adios!