ገዛኸኝ ነብሮን ለማሥረሳት ?! ገዛኸኝ ነብሮ የተገደለው ለኢትዮጵያውያን ክብርና ነፃነት ነበር !


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ

ገዛኸኝ ነብሮን ለማሥረሳት ?!
ገዛኸኝ ነብሮ የተገደለው ለኢትዮጵያውያን ክብርና ነፃነት ነበር ! …
*****//*****//*****

Image may contain: 1 person
ገዛኸኝ ነብሮ በሰለጠነ ቅጥረኛ ደቡብ አፍሪካ (ጆሃንስበርግ) ውስጥ ከተገደለ ሁለት ዓመቱ ሊመጣ ጥቂት ወራት ብቻ ቀሩት ! ነብሮን ለማስረሳት እየተደረገ ያለው ነገር ግን በእጅጉ የሚያስቆጭ ነው። ይህን ያልኩበትን ምክንያት በኋላ ላይ እመለስበታለሁ።
ነብሮ የተገደለው በሰለጠነ ቅጥረኛ ብቻ ሳይሆን ጊዜ በሚፈታው ውስብስብ ደባ ነው። በደባው ከአንድ አገር በላይ እንደተሳተፈበት ብዙ ማሳያዎች አሉ። አንዱ ጀግናው የአገር ልጅ ሕዝብ በሚበዛበት ካርልና ፖሊ ጎዳና ተገድሎ ፖሊስ ግን የደረሰው ከአርባ ደቂቃ በላይ #ሆን ብሎ በመዘግየት ነው። የምርመራው ሂደትም የባሰ ቁጭትና መንገብገብ የሚፈጥር ነው !
ገዛኸኝ ነብሮ የተገደለው ለኢትዮጵያውያን ክብርና ነፃነት ነበር ! …
*****//*****//*****
ጀግናው ከመገደሉ በፊት በነበረው ቀን በስፍራው በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በነበረ ዝግጅት ላይ ተገኝቶ ነበር። ተጠርቶ ሳይሆን ለመቶ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን እንደተለመደው በተቃውሞ የአጋርነት ድምጹን ለማሰማት ! አደረገውም ! ይህ ተቃውሞ የተለመደ ተግባሩ ነበር። ኢትዮጵያ ነፃ እስክትወጣ እቀጥልበታለሁም ይላቸው ነበር።
ነብሮ የቀድሞው 102ኛ አየር ወለድ ክፍለ ጦር አባልም ነበር። ባለነጠላጫማዎቹ አዲስ አበባን ተቆጣጥረው ባለብዙ ፎቆች ሲሆኑና ብዙዎችን በአደባባይ መግደል ሲጀምሩ ከአገር ወጥቶ ለሁለት አስርታት ያህል በተሰዋባት ደቡብ አፍሪካ ኖሯል።
ገዛኸኝ ነብሮ ከአገሩ እንደወጣ በደሙ ፍሰትና በሕዝብ ልጆች ሁለንተናዊ ትግል የአገሩ ነፃነት ቢረጋገጥም ለስንቱ ወንበዴ የተረፈች ቅድስት አገር አጽሙን በክብር ማሳረፍ አልቻለችም። ቤተሰቦቹ ልጃቸው እንዲረሳ በደቡብ አፍሪካ የሚገኙት የኢትዮጵያውያን ኮሙኒቲ አባላት ደባ እየፈጸሙ ለመሆኑ ያላቸውን ጥርጣሬና ቅሬታ ብዙ ማሳያዎችን በመጥቀስ ገልጸውልኛል። አሁንም ጊዜ አለ። ያለፈውን እየረሳን በዛሬ ሆያ ሆዬ መጠመዱ ይቆየንና የጀግናው አጽም እንዳይወቅሰን፣ ታሪክና ትውልድ እንዳይታዘበን አጽሙን በተሰዋላት አገሩ አፈር ላይ አሳርፉ !
ገዛኸኝ ነብሮ የተገደለው ለኢትዮጵያውያን ክብርና ነፃነት ነበር ! ..
*****//*****//*****

Image may contain: 7 people
በምስል#1_ ላይ አብረውኝ የምትመለከቷቸው የጀግናው እናት፣ ወንድምና እህቶች ሲሆኑ በቀድሞው የ102ኛ ክፍለ ጦር በራሪ ነብር ዓመታዊ ክብረ በዓል ላይ ተገናኝተን ጥቂት ካወጋን በኋላ የተነሳነው ሲሆን ምስል#2_ ለገዛኸኝ ነብሮ ክብር በበዓሉ ላይ የቀድሞ የትግል አጋሮቹ ያዘጋጁለት ምስል ነው።
ጀግኖቻችንን አንርሳ !
ነብሮን አታረሳሱ !!
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይጠብቅ !