ብአዴን/አዴፓ በብልጽግና ስም ተሸፋፍኖ የራሱን ወንጀል በሕወሓት እየደበቀ ሊኖር ይፈልጋል።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ብአዴን/አዴፓ በብልጽግና ስም ተሸፋፍኖ የራሱን ወንጀል በሕወሓት እየደበቀ ሊኖር ይፈልጋል። ገና ፖለቲካን ያልባነነው አማራ ክልል ላይ በመንደርተኝነት እየተደራጀ ያለው የፖለቲካ አሽከሩ ብአዴን/አዴፓ ለክልሉም ሆነ ለክልሉ ነዋሪ አንዳችም ነገር በተግባር ሳይሰራ በለውጥ ስም በወሬ ብቻ ራሱን ማኮፈስ ይዟል። የክልሉን ባለሐብቶች ገንዘብ እየሰበሰበ የባለሐብቶችን ሕገወጥ ንግድ በመመሳጠር እየደገፈ ለክልሉ ድሕነትን እንጂ እድገትን አላመጣም።

የሰኔ 15 2011 ጉድ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ሁከትና ሽብር በክልሉ ላለመፈጸሙ ምን ዋስትና አለ ? የሞጣው አይነት ሃይማኖት ላይ የተቃጣ ጥቃት በድጋሚ ላለመፈጸሙ ምን አይነት ዋስትና አለ ? የክልሉ ገዢ ፓርቲ ሰዎችና ተቋማት ላይ ከመጠቋቆሙ በፊት መረጃና ማስረጃ ካለው ሰዎቹንና ተቋማቱን ለፍርድ ለምን አያቀርብም ? ለሕዝብስ ለምን ይፋ አያደርግም ? ይህ መልስ ያልተገኘለት የፓርቲው የሌሎችን ስም ማጥፋት በራሱ መንግስታዊ ወንጀል ነው።

በአማራ ክልል የሚገኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ላይ ሽብር ለመፈጸም ሴራ ከማቀድና ለመተግበር ከመሮጡ በፊት ለሕዝብ የሚበጁና ከፖለቲካ አሽከርነቱ ነጻ የሚያወጡ ተግባራዊ ስራዎች ቢሰራ የተመረጠ ይሆናል።የክልሉ ፖለቲከኞችና ባለሐብቶች ለፖለቲካ ፍጆታ እና ለሕገወጥ ሸቀጦች ማራገፊያ ሲሉ የሚፈጽሙትን ሕገወጥ ድርጊት ሊያቆሙ ይገባል።

ምርጫው እስካልተጭበረበረ ድረስ አማራ ክልል ላይ ብአዴን/አዴፓ አያሸንፍም። ይህንንም ስለሚያውቅ የተቃዋሚ ድርጅቶች ላይ ሽብር ለመፍጠር እቅድ ነድፎ እየተንቀሳቀሰ ነው። ይህንን እቅዱን በጨረፍታ በብልጽግና ፓርቲ መሪ ሃሳብ ላይ ክልሉን ጠቅሶ ይፋ አድርጓል።

የሰለጠነ ፖለቲካ ትርጉም ያልገባው ብአዴን/አዴፓ በራሱ የማይተማመንና ሆዳም አመራሮች የተሞሉበት ስለሆነ ባለፉት ሶስት አስርተ አመታት ይህ ነው የሚባል የሰራው አንድም ሕዝባዊ ስራ የለም። በጨነቀው ሰዓት እየተነሳ ከሚረጨው አደንዛዥ ፕሮፓጋንዳ ውጪ ለሕዝብ ይህ ነው የሚባል ስራ አልሰራም። ብአዴን/አዴፓ በብልጽግና ስም ተሸፋፍኖ የራሱን ወንጀል በሕወሓት እየደበቀ የመኖር ስልቱን ሊያቆም ይገባል። #Miniliksalsawi