ዩንቨርስቲዎች ውስጥ ያለው አለመረጋጋትና ግድያ በነማን እንደሚመራ መንግስት በቂ መረጃ አለው።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ዩንቨርስቲዎች ውስጥ ያለው አለመረጋጋትና ግድያ በነማን እንደሚመራ መንግስት በቂ መረጃ አለው።

መፍትሔውም በእጁ አለ ! Minilik Salsawi

ከበቂም በላይ እጅግ የሚያስደነግጥ መረጃና ማስረጃ በእጁ አለው። ጥቂት በሕዝብ ላይ ቁማር የሚጫወቱ የመንግስት መዋቅር ባለስልጣናት፣ ፖለቲከኞችና በየጉሮኖው ዩንቨርስቲዎችን ያቋቋሙ ባለሐብቶች፣ የቀድሞ ጥቅማቸው የተገፈፈባቸው ግለሰቦች እና በገንዘብ የተደለሉ የዩንቨርስቲ መምሕራንና አስተዳዳሪዎች በዩንቨርስቲ ውስጥ ለሚነሱ ችግሮች ተጠያቂ ወንጀለኞች እንደሆኑ መንግስት በቂ መረጃና ማስረጃ በእጁ አለ።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እና የፌዴራል ፖሊስ እንዲሁም አቃቢ ሕግ ጥቂት የመንግስት መዋቅር ለግጭት የሚያውሉ ከፍተኛ ባለስልጣናትን ወንጀል ለመሸፈን ሲሉ የባለሐብቶችን ገበና ላለማጋለጥ ሲሉ የሐገሪቷን ሰላም እያደፈረሱ የደሐውን ልጅ ደም በየመንገዱ እንዲፈስ እያደረጉ ከመሆኑም በላይ ትውልዱን እየገደሉ ነው።

ይህ አትኩሮት የተነፈገው ትኩሳት እንዲበርድ ሁሉም መስራት ሲገባው የሕግ የበላይነትን በመደፍጠጥ ሌላ ጥፋቶች እንዲስፋፉና ዩንቨርስቲዎች እንዲዘጉ እየተደረገ ነው።

በተማሪዎች ግድያና በዩንቨርስቲ ሰላም መደፍረስ ላይ የሚሰሩ ፖለቲከኞችና ባለሐብቶች ከነተባባሪዎቻቸው መንግስት ይፋ ያድርግ ። መንግስት በአስቸኳይ ወንጀለኞችን ለሕዝብ ይፋ ማድረግ አለበት። #MinilikSalsawi