ድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ከ3ኛ ፎቅ ተማሪ ተወርውሮ መገደሉን ተከትሉ ላልተወሰነ ጊዜ ተዘጋ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ለድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ
ዩኒቨርሲቲያችን ሰኞ ታህሳስ 20/2012 ዓ/ም ሊጀመር የነበረው ትምህርት ባጋጠመን ወቅታዊ ችግር ምክንያት በዩኒቨርሲቲያችን ትምህርት ማስቀጠል የሚያስችል ሁኔታ አለመኖሩን ተረድቷል::

ስለሆነም የመማር ማስተማር ሂደቱ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቋረጥ የዩኒቨርሲቲ ሴኔት ወስኗል:: ስለሆነም ዩኒቨርሲቲው ከታህሳስ 20/2012 ዓ/ም በኋላ ምንም አይነት አገልግሎት የማይሰጥ መሆኑን እየገለጽን የተማሪዎችን የመልሶ መቀበያ ጊዜ ወደ ፊት በሚዲያ የሚገልጽ መሆኑን ወስኗል::

Image

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የ3ኛ አመት ተማሪ ከ3ኛ ፎቅ ህንፃው ተወርውሮ በመሞቱ እስከሚቀጥለው ድረስ ተጨማሪ ማስተማሪያ የመማር ማስተማር ሂደቱን አቁሟል ፡፡ ይሁኔ አለማየሁ የ3 ኛ ዓመት የባንክ ተማሪ ነበር።በሁለት ወራት ውስጥ በተመሳሳይ ከፎቅ ተወርውሮ ተማሪ ውስጥ ሲገደል 2ኛ ጊዜ ነው ፡፡

Image

Image

የሟች ተማሪ አስከሬን በነገው እለት ወደ ወለጋ ጉሊሶ የሚላክ መሆኑ ታውቋል ። ተማሪ ይሁኔ ከሞተ በኋላ በዩንቨርስቲው ውስጥና ውጪ ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል። በርካታ ተማሪዎች ዩንቨርስቲውን ለቀው የወጡ ሲሆን ከፊሎቹ ቀደም ብለው የገብርኤልን አመታዊ ንግስ ለማንገስ ወደ ቁልቢ ተጉዘዋል።