የአሜሪካ ኮንግረስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከስልጣን የማስወገድ ውሳኔን ደገፈ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የአሜሪካ ኮንግረስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከስልጣን የማስወገድ ውሳኔን ደገፈ

ፕሬዝዳንቱ ሁለት ክሶች ቀርበውባቸው ከስልጣናቸው እንዲነሱ የቀረበውን ሐሳብ የኮንግረሱ አባላት በአብላጫ አጽድቀውታል ።

impeachment ማለት በስልጣን ላይ ያለ ፕሬዝዳንት ጥፋት እጥፍተሀል ተብሎ 435 አባለት ባሉት በተወካዮች ምክርቤቱ (House of Representatives /congress) ክስ ሲቀርብበት ማለት ነው።በአሜሪካን ህገመንግስት በስልጣን ላይ ያለን ፕሬዚዳንት የመክሰስ ብቸኛ ስልጣን ያለው የተወካዮች ምክርቤት (House of Representatives ) ብቻ ነው።ፕሬዚዳንቱ ይከሰስ የሚለውን በምክርቤቱ ለመወስን ደግሞ ቢያንስ 216 የተወካዮች ምክርቤት አባላትን ድምጽ ማግኝት ይኖርበታል

የተወካዮች ምክርቤት (House of Representatives )ዛሬ ትራምፕን በሁለት ወንጀል ከሶታል አንደኛው ስልጣንን ያለአግባብ መጠቀም ( abuse of power) ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የተወካዮች ምክርቤት ሰራውን በትክክል እንዳይሰራ በማወክ ወይም እንቅፋት በመሆን (obstruction of Congress) ናቸው።ፕሬዝዳንቱ የተከሰሰበት ወንጀል 100 አባላት ላሉት ለሕግ መወሰኛ ምክር ቤት (senate) ቀርቦ ክሱ ይሰማል። በህግ መወሰኛው ምክርቤት ካሉት ከመቶ ሴናተሮች 75ቱ ፕሬዚዳንቱ በተከሰሰበት ክስ ጥፋተኛ ነው ብለው ድምጽ ከሰጡ ፕሬዚዳንቱ ከስልጣን ይወርዳል ማለት ነው።በአሜሪካን ሀገር በ230 አመት ታሪክ ፕሬዚዳንት ከሆኑት 45 ፕሬዝዳንቶች 3 ፕሬዝዳንት ብቻ ናቸው በተወካዮች ምክርቤት (House of Representatives ) ክስ ቀርቦባቸው ጉዳያቸውን ለመጨረሻ ጊዜ ለመወሰን ወደ ሕግ መወሰኛ ምክር ቤት (senate) የተላከው አንደኛው ፕሬዝዳንት Andrew Johnson በ1868 ሌላው ፕሬዝዳንት Bill Clinton in 1998 ሶስተኛው ደግሞ  አሁን በስልጣን ላይ ያለው ፕሬዝዳንት Donald John Trump ናቸው

በJuly 1974 ፕሬዝዳንት Nixon በተወካዮች ምክርቤት (House of Representatives ) በሶስት ክስ ተከሰው ገና ሙሉ ምክርቤቱ ድምጽ ሰጥቶበት ወደ ሕግ መወሰኛ ምክር ቤት (senate) ሳይላክ ፕሬዝዳንት Nixon በፈቃዱ ከስልጣን ወርዶአል። ምንም እንኩዋን ፕሬዝዳንት Andrew Johnson እና ፕሬዝዳንት Bill Clinton በተወካዮች ምክርቤት (House of Representatives ) ክስ ቀርቦባቸው ጉዳያቸው ወደ ሕግ መወሰኛ ምክር ቤት (senate) ቢደርስም የሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ ሁለቱንም ፕሬዝዳንቶች የቀረበባቸው ክስ በቂ አይደለም / ጥፋተኛ አይደሉም ብሎ ለቆአቸዋል

ዛሬ የፕሬዝዳንት ትራምፕ ክስ በተወካዮች ምክርቤት ለሕግ መወሰኛ ምክር ቤት (senate) ቢቀርብም የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት (senate) በበላይነት የተቆጣጠረው የራሳቸው የፕሬዝዳንት ትራምፕ የሪፐብሊካን ፓርቲ ስለሆነ ይህ ክስ ውድቅ የመሆን እድሉ ሰፊ ነው ተብሎ ይታመናል

ዲሞክራቶች በሚቆጣጠሩት የአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተደረገው ክርክር ፕሬዚዳንት ትራምፕ ስልጣናቸውን ያለአግባብ ተጠቅመዋል በሚል 216 ለ197 ድጋፍ ሲያገኝ፣ የኮንግረሱን ሥራ አደናቅፈዋል በሚል የቀረበባቸውን ክስ ደግሞ 230 ለ198 በኾነ ድምጽ ነው ፕሬዝዳንቱ ከስልጣናቸው እንዲነሱ የቀረበውን ውሳኔ ምክር ቤቱ የተቀበለው ።

ጉዳዩ ሪፐብሊካኖች በሚበዙበት የላይኛው ምክር ቤት ሴኔት ሄዶ በቀጣዩ ወር ክርክር ተደርጎበት ተቀባይነት ካገኘ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከስልጣናቸው እንዲወገዱ በኮንግረሱ የተላለፈው ውሳኔ እውን ይኾናል ።

ይኽም ሂደቱ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በአሜሪካ ታሪክ የስልጣን ዘመኑን ሳይጨርስ በህግ አውጪው አካል ስልጣኑን እንዲለቅ የተወሰነባቸው ሶስተኛው ፕሬዝዳንት ያደርጋቸዋል።