የንግድ ባንክ የውጭ ምንዛሬ ተመን አንድ ዶላር ወደ 32.22 የኢትዮጵያ ብር ደርሷል፡፡


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በዛሬው የንግድ ባንክ የውጭ ምንዛሬ ተመን አንድ ዶላር ወደ 32.22 የኢትዮጵያ ብር ይመነዘራል። በአንድ ወር ውስጥ ብቻ ከነበረበት 29 ብር አካባቢ ወደ 32.22 ደርሷል፡፡ ይህም ማለት ወደ አስር ፐርሰንት አካባቢ ጨምሯል ማለት ነው፡፡ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ገበያው የመሪነቱን ሚና እየተጫወት መሄዱን እና የውጭ ምንዛሬ ገበያው ነጻ ለመሆን እየተንደረደረ ለመሆኑ አንዱ ማሳያ መንገድ ነው፡፡

በአንድ ወቅት ጎረቤት አገር ኬንያ ከፍተኛ የሆነ የዶላር እጥረት ሲያጋጥማት አንድ መላ ዘየደች። የዶላር ገበያውን ነጻ አደረገቸው፡፡

ወዲያው መንግሰት በገበያው ሃይል ላይ የተንተራሰ የውጭ ምንዛሬ ተመን መተገበር ጀመረ፡፡ በዚህ ጊዜ በመንግስት ጡንቻ ስር ሆነው ተፈላጊውን የዶላር ምንጭ ማምጣት ያልቻሉት የገበያ ትስስሮች ነጻ ሆነው በገበያው ላይ መሰረታቸውን ሲጥሉ ቀስ በቀስ በፍላጎቱና በአቅርቦት መካከል ሚዛን መፍጠር ጀመሩ፡፡ በአሁን ወቅት ለኬንያ ኢኮኖሚ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ተፈላጊውን ምርታማነት አያሳጣቸውም፡፡ እንደውም በባንክ ያለውና በጥቁር ገበያው ያለው የምንዛሬ ተመን ተመሳሳይ ነው፡፡

በተቃራኒው ኢትዮጵያ ላይ በውጭ ምንዛሬ እጥረት አያሌ ኢንቨስትመንቶች ሲቆሙና መጨረስ ባለባችው ሰዓት አልቀው ወደ ማምረት አግልገሎት እንዳይገቡ ጋሬጣ ሆኖባቸው ቆይቷል፡፡ በታቀደላቸው የጉዜ ሰሌዳ ስራ አጥነትን ይፈታሉ የተባሉ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች ሲባክኑ ይስተዋላል።

እንደ አገር የግብርና ምርት ላይ እንደተመሰረተ ምጣኔ ሀብት የዶላር ተመን ጭማሬው እንደ አገር የወጪ ንግድ ገቢያውን፤ ብሎም የንግድ ሚዛኑንና ጠቅላላ የክፍያ ሚዛኑን ሊያንገዳግደው ይችላል። በመሆኑም ለጊዜውም ቢሆን የማክሮ ኢኮኖሞ ኢምባላንስ ሊፈጥር ይችላል። ይሁን እንጂ ችግሩ ጊዜአዊ ነው። መንግሰት ይህን የገበያ ማዕከል ነጻ ካደረገው በቅርብ ጊዜ ውስጥ ተፋለጊውን የዶላር ክምችት ማግኘት ይችላል፡፡

በተጨማሪም ብሄራዊ ባንክ ለዲያስቦራ ኢትዮጵያዊያን የፈቀደውን በዶላር ጥሪትን የማሰቀመጥ ህግ ለአገር ውስጥ ነዋሪዎች ቢፈቅድ ደግሞ ተጨማሪ የውጭ ምንዛሬ ክምችት ማግኘት ይቻላል፡፡ በህገ ወጥ መንገድ ወደ ውጭ አገር የሚወጣውን የዶላር መጠንም በእጅጉ ማሳነስ ይችላል ብዬ አምናለው፡፡

ምክንያቱም አንድ የማንኛውም አገር ባለሀብት ዶላር ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲያስቀምጥ ካተፈቀደለት ዓይኔ እያየ በኢትዮጵያ ብር አስቀምጬ የመግዛት አቅሙ ከሚቀንሰ በሚል ስሌት ወደማይሆን ህገ ወጥ ተግባር ተሰማርቶ በህገ ወጥ መንገድ ገንዘቡን ያሸሻል፡፡ ይህ ብቻ አይደለም ይህን ፖሊሲ መተግባር ቢቻል ጎረቤት አገር ያሉና አገራቸው በተለየያ ምክንያት ገንዘባቸውን ማሰቀመጥ የማይፈልጉ የጎረቤት አገር ሰዎች ዓይናቸውን በቅርብ ወደምትገኘው ወደ ኢትዮጵያ ያደርጋሉ፡፡

ይህም ለተሳለጠ የውጭ ንግድ እንቅስቃሴ አዎንታዊ ሚና ይኖረዋል። ስለሆነም መንግሰት አሁን ላይ እየተከተለ ያለው ገበያ ተኮር (market oriented) አካሄድ አበረታቶ በመጠኑ መስመሩን እስኪይዝ አስፈላጊውን ቁጥጥር እያደረገ መሄድ መቻል አለበት፡፡