“የተወሰኑ ሰዎች በፈጠራ ወሬ አገር ሲያተራምሱ ዝም ማለት ተገቢ አይደለም” ኡስታዝ አህመዲን ጀበል


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


“የተወሰኑ ሰዎች በፈጠራ ወሬ አገር ሲያተራምሱ ዝም ማለት ተገቢ አይደለም” ኡስታዝ አህመዲን ጀበል የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ

(ኢ.ፕ.ድ)

የተወሰኑ ግለሰቦች የማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም በፈጠራ ወሬ አገር ሲያተራምሱና ግጭት ሲያቀጣጥሉ እየታየ ዝም ሊባል እንደማይገባ የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ገለፀ፡፡

ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፀው፣ ከ100 እና 200 የማይበልጡ ሰዎች በማህበራዊ ሚዲያ በመጠቀም ችግር ሲፈጥሩ ዝም ከተባለ ነገ ከባድ ችግር ይፈጠራል፡፡ እነዚህ ግለሰቦች እውነትነት የሌለው የፈጠራ ወሬ ዜና አድርገው በማህበራዊ ሚዲያ ሲያሰራጩ የት ሆኖ እንደጻፉትና እንደለጠፉት (ፖስት እንዳደረጉት) በቀላሉ መለየት የሚቻልበት ቴክኖሎጂ እያለ ብሄርን፣ሀይማኖትን፣ተቋማትንና ግለሰብን ስም ሲያጠፉና ሲሰድቡ ዝም ብሎ መመልከት ተገቢ አይደለም፡፡ አጥፊውን በህግ ተጠያቂ እንዲሆን በማድረግ ሌላውን ማህበረሰብ ማስተማር ያስፈልጋል፡፡
ለተጨማሪ ንባብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/Ama/?p=23463