“የጠቅላይ ሚኒስትሩና የመከላከያ ሚኒስትሩ መቃቃር ውሎ አድሯል” የቱለማ አባ ገዳ


ኢትዮጵያን ካጋጠሟት እጅግ ውስብስብ ችግሮች ለማዳን የተለያዩ ጠቃሚ ሃሳቦችን እና ገንቢ ትችቶችን የሚያቀርቡ ነፃ ሚዲያዎች ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ይታወቃል። ስለዚህም ኢትዮ360፣ መረጃ ቲቪ፣ አዲስ ድምጽ፣ ምንሊክ ቲቪ እና ሌሎችም የኢትዮጵያዊነት አጀንዳ የሚያራምዱ ሚዲያዎች በመተባበር ፕሮግራሞቻቸውን በሳተላይት ቲቪ ለኢትዮጵያ ህዝብ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ሚዲያዎች የፈጠሩት ማህበር የሳተላይት ወጪውን መሸፈን እንዲያስችለው ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ ከፍተናል → እዚህ ሊንክ ላይ ይጫኑ። ለትብብርዎ እናመሰግናለን።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ እና የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ለማ መገርሳ ግንኙነት መሻከር ከጀመረ ውሎ ማደሩን፤ እነሱም ጉዳዩን የሰሙት ከአምስት ወራት ገደማ በፊት እንደሆነ የቱለማ አባ ገዳ ጎበና ሆላ ለቢቢሲ ገልፀዋል።

“እነዚህ የአባ ገዳ ልጆች በፊት ምን ያህል ይቀራረቡ እንደነበር እየተራራቁ እንዳሉ የሰማነው ከአምስት ወር በፊት ነው” የሚሉት አባ ገዳ ጎበና ይህ ለኦሮሞ ህዝብ ጥሩ እንዳልሆነ ትግሉንም ወደ ኋላ እንደሚመልስ ስጋታቸውን ይገልፃሉ።

አባ ገዳ ጎበና እንደሚሉት ሁለቱ መሪዎች መካከል ንፋስ መግባቱን ሲሰሙ ከኦሮሞ ምሁራን፣ የሃይማኖት መሪዎችና አባ ገዳዎችም አንድ ላይ ሆነው ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይንም ሆነ መከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ለማን በተናጠልም ሆነ አንድ ላይ ለማግኘት ያደረጉት ሙከራ ሳይሳካ ቀርቷል።

ያለፈው አልፏል አሁንም ወደፊት የሚቀር ብዙ ስለሆነ ሁቱንም ማግኘት አስፈላጊ ነው ብለው እንደሚያስቡም ገልፀዋል አባ ገዳው።

በመሪዎቹ ዘንድ የእናንተ ተሰሚነት ምን ያህል ነው? የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው አባ ገዳ ጎበና “ለኦሮሞ ህዝብ እንዳላቸው ቅርበት የሚቀበሉትም የማይቀበሉትም አለ። አባ ገዳዎችን የሚፈልጉበት፣ የሚጠቀሙበትና የሚንቁበት ቦታ እንዳለ ለማንም ግልፅ ነው” ነበር መልሳቸው።

በመጨረሻም ‘እንኳንስ አብሮ የሚሰራ ሰው እግር እና እግር እንኳ ይጋጫል’ የሚሉት አባ ገዳ ጎበና ችግሩ ይፈታል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትርና የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ለማ መገርሳ፤ የኢሕአዴግን ውህደት እንደማያምኑበት ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ መግለፃቸው ይታወቃል።

“መዋሀዱ ትክክል አይደለም። ከሆነም በችኮላ መሆን የለበትም፤ ወቅቱም አይደለም” ያሉት አቶ ለማ፤ በመደመር ፍልስፍናም እንደማይስማሙ ከራድዮ ጣቢያው ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ መናገራቸው ተዘግቧል።

አቶ ለማ፤ የኢሕአዴግ ምክር ቤት የፓርቲዎችን ውህደት ባፀደቀ ጊዜ የምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ ተገኝተው እንደነበር አስታውቀው ስለ ሂደቱ ግን ለጣቢያው ከማብራራት ተቆጥበዋል።

አቶ ለማ መደመርን የተቃወሙበትን ምክንያት ለቪኦኤ ሲያስረዱም፤ በአጠቃላይ ከመጀመሪያ ጀምሮ እስከ መጨረሻ ድረስ የፓርቲዎች ውህደትን በተመለከተ የተለየ ሀሳብ እንዳላቸው ተናግረዋል።

ቢቢሲ