አዲስ አበባ ላይ ባልደራሱ የቀድሞውን ቅንጅት ይተካ ይሆን ???


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


አዲስ አበባ ላይ ባልደራሱ የቀድሞውን ቅንጅት ይተካ ይሆን ??? ( ምንሊክ ሳልሳዊ )

ራሱን ባለአደራ ቦርድ ብሎ የሚጠራው ስብስብ ወደ ፖለቲካ ድርጅትነት እንዲቀየር የዲያስፖራው ጫና መጀመሩን ሰምተናል። ዲሲ የሚገኘው የአንድነት ኃይሉ የፖለቲካ ተፅእኖ በመፍጠር ደረጃ የተሳካለት ስብስብ ነው።

ወደ ፖለቲካው አለም ከመጣ እስክንድር ነጋ አዲስ አበቤውን፣ የዲያስፖራውን ኃይል ይዞ ከኢዜማ ጋር አዲስ አበባን ሊቆጣጠር ይችላል። እንደኔ ከፖለቲከኝነት ይልቅ ባልደራሱ በሲቪክ ማሕበርነት ራሱን ቢያሳድግ ለጨቋኞች ትልቅ አደጋ ቢሆን የተመረጠ ይሆናል።

ምርጫውን ከገዢው ፓርቲ ውጪ ኃይሎች ሊያሸንፉ ይችላሉ በሚል የ አዲስ አበባ ከተማ ጥቅሞችና አስፈላጊ ገቢዎች ወደ ፌዴራሉና ኦሮሚያ ክልል እየዞሩ ነው። ይህ ሕወሓት በዘጠና ሰባት ምርጫ የወሰደው የድንጋጤ እርምጃ ነበር፤ አሁን እየተደገመ ነው። ገዢው ፓርቲ ከልብ መደናበሩንና መደንገጡን እያየን ነው።

የባልደራሱም እርምጃ ፈርና ሕግን የተከተለ በመኦኑ አሸናፊነቱን ከጅምሩ ያረጋገጠበት ነው። በአንድ ብሔር አቀንቃኝነትና በኃይማኖት ጉዳዮች ባልደራሱ በጽንፈኛ ብሔርተኞች በፈጠራ ስሙ እንዳይጠፋ ጠንካራ ስራዎች ሊሰራ ይገባል። ቀደም ባሉ ጊዜያት የፖለቲካ ፓርቲዎችን ሲበጠብጡ፣ ሲያፈርሱና ሲያስደንሱ የነበሩ የደሕንነት ቅጥረኞችን ከመሐሉ ጎትቶ አውጥቶ ቢያስወግድ የተሻለ ነው። ( ምንሊክ ሳልሳዊ )