" /> ኢትዮጵያዊው የባህል አምባሳደር መላኩ በላይ ተሸለመ። | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

ኢትዮጵያዊው የባህል አምባሳደር መላኩ በላይ ተሸለመ።

ኢትዮጵያዊው የባህል አምባሳደር ተሸለመ።

በየዓመቱ በሞሮኮ ራባት ከተማ በሚካሄደው ቪዛ ፎር ሚውዚክ ፌስቲቫል (visa for Music ) ኢትዮጵያዊው የባህል አምባሳደር መላኩ በላይ ተሸለመ።

እ.ኤ.አ. በ2013 የተጀመረው ይህ የሙዚቃ ፌስቲቫል በአፍሪካና በመካከለኛው ምስራቅ በሙዚቃ ዘርፍ ተጽኖ የፈጠሩ ሰዎችን ይሸልማል።
ዘንድሮም ለ6ኛ ጊዜ በተዘጋጀው በዚህ ፌስቲቫል የፈንድቃ ጥበባ ባህል ማዕከል ባለቤትና “የኢትዮ ከለር “የባህል ሙዚቃ ባንድ መስራች አርቲስት መላኩ በላይ ተሸላሚ ሆኗል።

የፓን አፍሪካኒዝም ሀሳብ አቀንቃኝ እንደሆነ የሚነገርለት ሞሮኳዊው ኢብራሒም ኤል ማዝነድ / Brahim El Mazned /የሽልማት ድርጅቱ መስራች ሲሆን “የየሀገሩ ሙዚቃን በማወቅና በመረዳት ሰብአዊነትን ማዳበር ይቻላል።” ብሎ ያምናል ።


ምንጭ፦Visa For Music


የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV