የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ለመላው ሙስሊም ኢትዮጵያዊ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት መግለጫ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በመጭው ቅዳሜ የሚከበረውን 1494 ኛውን የመውሊድ በዓል አስመልክቶ ለመላው ሙስሊም ኢትዮጵያዊ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ። ምክር ቤቱ ነብዩ ሙሃመድ አንድነትን ያስተማሩ፣ ህዝባቸውን በወንድማማችነት ያስተሳሰሩ፣ ጥላቻን አውግዘው ፍቅርንና ሰላምን አብዝተው የሰበኩ ናቸው።

መውሊዱም በሃገራችን ጨምሮ በዓለማት በብሔራዊ ደረጃ የመከበረል ምክንያት ይሄው ነው ብሏል። ምክር ቤቱ ከፌደራሉ ጀምሮ የክልል እና የከተማ መስተዳድር መጅሊሶችን እያዋቀረ ቢሆንም ማዕከልን ባልጠበቀ አኲኋን የመጅሊስ ምክር ቤቶችንና እና መስጅዶችን የመንጠቅ በከተሞች ኢማሞችንና ሙአዚኖችን ፤ በገጠር መሻኢኮችንና ሙደሪሶችን ያማስከፋት፣ ከስራ የማፈናቀል ድርጊት ገጥሞኛል ብሏል

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር ኢድሪስ ለእምነቱ ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ በኢትዮጵያ በዚህ ዓመት የሙስሊም አንድነት ብለን የጀመርነው ስራ ” በዓለም የሌለ አንድነት ነው” ብለዋል። የሃይማኖት ልዩነት ያላቸው ሰዎች በዓለም አንዱ የበላይ አንዱ የበታች ሆኖ ይኖራል እንጅ ሁለቱ በአንድ ቢሮ አንድነህ ፈጥረው በሰላም መሄድ በእኛ ሃገር ብቻ የተጀመረ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ይህንን ነገር ስንጀምረው “ሰለፍያ” እና “ሱፊያ” የሚባሉ ነገሮች ነበሩ ያሉት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር ሁለቱም እኩል ሆኖ እንዲመራ ነው ያደረግነው።አሁን ግን በኦሮሚያ ስንሄድ በአጠቃላይ ሰለፍያ ብቻ ነው የተመረጠው ይህም ችግር መስተካከል አለበት ብለዋል። ችግሩ በደቡብም የተስተዋለ ቢሆንም ማስተካከላቸውንም አመልክተዋል። በሌላ በኩል በሃረሪ ፣ ሶማሌ እና ድሬዳዋ እኛ ከመመረጣችን በፊት የፊቱን መጅሊስ ገልብጦ ህገ ወጥ መጅሊስ ነው ያለው ያንንም ለማስተካከል ተዘጋጅተናል ብለዋል።

Source DW Amharic