የኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ፓርቲ ኢሀን ቀጣዩ 5ኛው አገራዊ ምርጫ እንዲራዘም ጠየቀ።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ ፓርቲ (ኢሀን) ቀጣዩ 5ኛው አገራዊ ምርጫ እንዲራዘም ጠየቀ።

ፓርቲው ከጥቅምት 21 ጀምሮ አገራዊ የፖለቲካ ፓርቲ ሆኖ ከብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እውቅና ማግኘቱንም አስታውቋል።

የፓርቲው ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አገሪቱ ምርጫ ማካሄድ በምትችልበት ቁመና ላይ ባለመሆኗ ምርጫው አንዲራዘምለት ጠይቋል።

ህዝባዊ አስተዳደደር ለመትከል እና የተለያዩ የፖለቲካ ሀሳብ አማራጮችን ለህዝብ አቅርቦ ህዝቡ የፈለገውን እንዲመርጥ ፣ በቅድሚያ የዜጎች ሙሉ ነፃነት ማክበርና ማስከበር ያስፈልጋል ብሏል ፓርቲው በመግለጫው፡፡

ነፃነት ማለት በእራሱ የአማራጮች መኖር ማለት ነው ፣ ስለሆነም ነፃነት በሌለበት ምርጫ ሊኖር አይችልም ያለው ኢሃን መንግስት ምርጫውን አላራዝምም ካለ ግን በምርጫው መወዳደራቸንን እንቀጥላለን ብሏል።

ፓርቱው በመግለጫው አዲስ አበባ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን የጋራ ምልክታችን ናት ብሏል፡፡

የአዲስ አበባ እራስ በእራስ የማስተዳደር መብት እንዲከበር ፣ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ምልክት ሆና እንድትቀጥል ጠንክሮ እንደሚሰራ ፓርቲው ገልጿል፡፡

ሰሞኑን በኦሮሚያ ፣ በድሬድዋ ና በሐረር ማንነት መሰረት ባደረገ መልኩ በዜጎች ላይ የተፈፀመውን ዘግናኝ ጭፍጨፍ በገለልተኛ አካል ተጣርቶ ለህዝብ ይፋ እንዲደረግም ጠይቋል፡፡

Ethio FM