ግብጽ በዲፕሎማሲው መስክ የምታደርገው ግፊት አሸናፊነት የሕዳሴውን ግድብ ገደል እንዳይከተው ያሰጋል።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ግብጽ በዲፕሎማሲው መስክ የምታደርገው ግፊት አሸናፊነት የሕዳሴውን ግድብ ገደል እንዳይከተው ያሰጋል።

በዋሽንግተን የተደረገው የሕዳሴውን ግድብ የተመለከተው ድርድር እና መግለጫ የሚያመላክተው ነገር ቢኖር ግብጻ በዲፕሎማሲውና በፖለቲካው ረገድ አለም አቀፍ ጫና እና ተሰሚነቷን ነው።

መጀመሪያ ይህ ስብሰባ በአንድ የኃያላን አገር ፕሬዝዳንት አትኩሮት አግኝቶ ዲሲ ላይ ድርድር እንዲደረግና መግለጫ እንዲወጣ የዲፕሎማሲውን ስራ እንዲሰራ ያደረገችው ግብፅ ናት።በዚህ ድርድር ላይ ለወደፊቱ በሚደረጉ ውይይቶች ድርድሮችና ንግ ግሮች ላይ ጫና ሊያሳድሩ የሚችሉ አሜሪካና ዓለም ባንክን የመሳሰሉ ሶስተኛ ወገኖች በግብጽ ጫናና ፍላጎት በታዛቢነት መመረጣቸው ለኢትዮጵያ ጥንካሬ ትልቅ አደጋ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል።

ሁለተኛ ደረጃ ግብጽ የቀደሙትንና በኢትዮጵያ ተቀባይነት ያጡትን ስምምነቶች ተግባራዊ እንዲደረጉ ግፊት በማድረግ አሜሪካና ዓለም ባንክ ታዛቢ እንዲሆኑ ያደረገችው ጫና ተቀባይነት አግኝቷል። ኢትዮጵያ ማንም ሶስተኛ ወገን በ አደራዳሪነትም ሆነ በታዛቢነት አልቀበልም ያለችውን አቋሟን እንድትቀይር በግብጽ ግፊት አሜሪካ ጫና አሳድራለች።

ትናንት ከተካሄደው መርሃ ግብር ቀደም ብሎ የግብጽ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሳሚህ ሽኩሪ ከፕሬዝደንት ትራምፕ ከፍተኛ አማካሪ ጃሬድ ኩሽነር ጋር ውይይት ማድረጋቸውን የግብጽ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ቢሮ አስታውቋል። ግብፆች ብዙ ነገሮችን ጮክ አድርገው ቀውስ እንዳለ አድርገው ስለሚያወሩና ስለሚያስወሩ ወዳጅ አገሮች ይህ ያሳስባቸዋል።ይህ የሚያሳየው ምን ያሕል የዲፕሎማሲ ስራ በግብፅ መሰራቱን ነው።

የኢትዮጵያ መንግስት በዲፕሎማሲው በኩል ከግብፅ የበለጠ ጉዳዩን በማጮህ ግብፆችን መቅበር እየቻለ የሔደበት አካሔድ ለሕዳሴ ግድቡ መሞት ትልቅ ስጋት ሆኗል። ካሁን በፊት ኢትዮጵያ አልስማማም እያለች የሔደችበት መንገድ በነትራምፕ ጫና የመስመር ለውጥ እንድታደር ያደርጋታል።በዲሲ ያለው የኢትዮጵያ ልዑክ በጭንቀት መወጠሩ ሌላም ጥያቄዎችን ያስነሳል። #MinilikSalsawi