የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በሁሉም ቋንቋ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ማሰልጠኛ ማዕከል እንዲከፈት ወሰነ፡፡


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በሁሉም ቋንቋ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ማሰልጠኛ ማዕከል እንዲከፈት ወሰነ፡፡

(አብመድ) ከጥቅምት 12 ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ 14 ያህል ነጥቦችን ያካተተ መግለጫ አውጥቷል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶሱ በመክፈቻ ንግግር የቀረበው መልዕክት ለቀጣይ የቤተ ክርስቲያኗ መንፈሳዊና ማኅበራዊ ተልዕኮ ጠቃሚ መሆኑን በማመላከት ማጽደቁንም አስታውቋል፡፡

በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ሠላም ዙሪያም መግለጫ የሰጠው ሲኖዶሱ ‹‹በኢትዮጵያ እየታዬ ያለው የሰው ሕይወት መጥፋትና የዜጎች ንብረት መውደም ቅዱስ ሲኖዶሱን ያሳዘነ ሲሆን መንግሥት ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ ሠላም እንዲያስከብር፣ የዜጎች ደኅንነት እንዲጠበቅ እንዲያደርግ፣ የተፈናቀሉትም ወደ ቀያቸው እንዲመለሱና ለጠፋው ንብረታቸው ማቋቋሚያ እንዲደረግላቸው፤ በተለይም በክርስቲያኖችና አብያተ ክርስቲያናት ላይ እየደረሰ ያለው ስደትና መከራ ጎልቶ እየታዬ በመሆኑ የጥፋቱ መልዕክተኞችን መንግሥት በሕግ እንዲጠየቁ እንዲያደርግ›› ብሏል፡፡

በኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች የተለያዬ ቋንቋ ተናጋሪዎች በብዛት እንደሚገኙ ያመለከተው የቅዱስ ሲኖዶሱ መግለጫ ‹‹የቤተ ክርስቲያኒቱን ተከታዮች በቋንቋቸው ማስተማርና ማገልገል እንዲቻል በየአህጉረ ስብከቶቹ የሚገኙ የአብነት ትምህርት ቤቶችን ማጠናከር፣ ከልዩ ልዩ ቋንቋ ተናጋሪዎች አገልጋዮችን ማፍራት እንዲቻል ለትምህርት ቤቶች ማጠናከሪያ የሚሆን ቋሚ በጀት እንዲመደብ፤ በቀጣይም በሁሉም አፍ መፍቻ ቋንቋ በማዕከል ማሰልጠኛ እንዲቋቋም›› ብሏል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶሱ የተጀመሩ ሀገራዊ የእርቅ ሂደቶች እንዲቀጥሉ፣ የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ሕዝባዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲጠናቀቅና የተጀመሩ ሀገራዊ ለውጦች እንዲጠናከሩ ማገዝ እንደሚገባም በመግለጫው አመላክቷል፡፡