ከስድስት ወር በላይ በመዲናዋ መሬት አጥሮ የሚያስቀምጥ ማንኛውም አካል መሬት ይወረሳል- ኢ/ር ታከለ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ከስድስት ወር በላይ በመዲናዋ መሬት አጥሮ የሚያስቀምጥ ማንኛውም አካል መሬት ይወረሳል- ኢ/ር ታከለ

(ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ከስድስት ወር በላይ መሬት አጥረው የሚያስቀምጡ የፌዴራልም ሆነ የክልል መንግስታት መሬት እንደሚወረስ ኢንጅነር ታከለ ኡማ አስታወቁ።

ኢንጅነር ታከለ ኡማ በአዲስ አበባ በዘጠኝ ክፍለ ከተማዎች የሚገነቡ ከ20 ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ አስጀምረዋል።

በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር ከስድስት ወር በላይ በከተማዋ ያለምን ግንባታ መሬት አጥሮ የሚያስቀምጥ ማንኛውም አካል መሬቱ እንደሚወረስበት ማረጋገጥ አፈልጋሉ ብለዋል።

ሀብት የሚባክንበት ወቅት አልፏል ያሉት ምክትል ከንቲባው፥ በእያንዳንዱ ቦታ በመንግስት እና በባለህብቶች ግንባታ ሳይካሄድባቸው ታጥረው የተቀመጡ መሬቶች በጥናት ተለይተዋል ብለዋል።

በመሆኑም ግንባታ ሳይካሄድባቸው የሚገኘት እነዚህ መሬቶች በቅርቡ ወደ መሬት ባንክ ይመለሳሉ ብለዋል።