በአርባምንጭ በሰበታ ህይወታቸውን ያጡ ወገኖችን ለማሰብ የታቀደው የሐዘን ቀን ተከለከለ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ከሰሞኑ የጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በሰበታ ህይወታቸውን ያጡ ወገኖችን ለማሰብ የሻማ ማብራት ፕሮግራም ጥቅምት 22 በጋሞ አደባባይ ለማዘጋጀት አቅዶና ጥሪ አድርጎ የነበረ ቢሆንም ኮማንድ ፖስቱ “የደረሰኝ ደብዳቤ የለም” ስለዚህ በእለቱ የሚከናወን የሀዘን ቀን የለም ብሏል!

ኮማንድ ፖስቱ የሀይል እርምጃ እንደሚወስድ አስጠነቀቀ!

ከሰሞኑን ጋዴፓ (ጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ) በሰበታ የተገደሉትን ወገኖችን ለማሰብ የሻማ ማብራት ፕረግራም ጥቅምት 22 በጋሞ አደባባይ ለማዘጋጀት አቅዶና ጥሪ አድርጎ የነበረ ቢሆንም ኮማንድ ፖስቱ ከልክሏል።

የጋሞ ዞን ክላስተር ጊዜያዊ የጸጥታ ኮማንድ ፖስት ምንም አይነት የሻማ ማብራት እና የጥቁር ሀዘን ቀን ስነ-ስርዓት በአርባምንጭ ከተማ እንዳልተፈቀደ ያሳወቀ ሲሆን ክልከላዬን ጥሶ የሚወጣ ማንኛውም አካል ላይ የሀይል እርምጃ እወስዳለው ሲል አስጠንቅቋል።

ምንጭ: የዞኑ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን

No photo description available.

No photo description available.