ጃዋር ሳይጠየቅ ፍትህ እናሰፍናለን ማለት ቀልድ ነው – ዶ/ር ስዩም መስፍን (የሰላም ሚኒስቴር ሚንስትር ዲኤታ)


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


“ጃዋር ሳይጠየቅ ፍትህ እናሰፍናለን ማለት ቀልድ ነው”
ዶክተር ስዩም መስፍን

የአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እና የሰላም ሚኒስቴር ሚንስትር ዲኤታ የሆኑት ዶክተር ስዩም መስፍን 78 ንጹሀን ዜጎች በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲገደሉ ምክንያት የሆነው አሸባሪው ጃዋር መሀመድ እና ግብረ አበሮቹ በህግ ሳይጠየቁ ሌሎችን በማሰር ፍትህ እናሰፍናለን ማለት ቀልድ ነው

ሲሉ አቃቤ ህግን ክፉኛ የተቹ ሲሆን “ጃዋርና ግብርአበሮቹ በህግ ባልተጠየቁበት ሀገርና ሁኔታ ስለ ህግ ማስከበር/መከበር ማንም ግለሰብ/የመንግስት ተቋም የመናገር ሞራል የለውም። በህግ የሚያስጠይቀው ቢያንስ ደግሞ ከሀገር የሚያስባርረው ብዙ ማስረጃዎች ያሉበት ወንጀለኛ በህግ አለመጠየቅ ፤ የአያሌ ንጹሀን ደም እንዲያፈስ ከመፍቀድ አይተናነስም።

አሁን ጃዋርና ግብርአበሮቹ በህግ ባልተጠየቁበት ሀገርና ሁኔታ ስለ ህግ ማስከበር/መከበር ማንም ግለሰብ/የመንግስት ተቋም የመናገር ሞራል የለውም። በህግ የሚያስጠይቀው ቢያንስ ደግሞ ከሀገር የሚያስባርረው ብዙ ማስረጃዎች ያሉበት ወንጀለኛ በህግ አለመጠየቅ ፤ የአያሌ ንጽሀን ደም እንዲያፈስ ከመፍቀድ አይተናነስም። እሱ ቆሞ እየሄደ፣ እንደፈለገው እየፈነጨ አቃቢ ህግ ሌሎችን የመክሰስ የማሰር የሞራልም የህግም ልእልና የለውም!!!! ግዜው አጠረም ረዘመም በህግ መጠየቁ ግን አይቀርም!!!!!!!