የጠቅላይ ሚኒስትሩ ባዶ በርሜሎች ቆርቆሮዎች


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የጠቅላይ ሚኒስትሩ ባዶ በርሜሎች ቆርቆሮዎች
ምንሊክ ሳልሳዊ – ስለግልፅነት እያወራን የበለጠ ሚስጥራዊ የምንሆን ከሆነ ያው መዋሸት ነው፡፡ ዛሬ ያልነውን ነገ ካልደገምነው ያው መዋሸታችን ነው፡፡ ሰውን በሸራ ኳስ እያጫወትን እኛ በካፖርተኒ የምንጫወት ከሆነ ያው ማጭበርበራችን ነው፡፡ በመዋሸት የተገነባ አመኔታ ውሎ አድሮ ያዋርዳል ፤ዋጋም ያስከፍላል።
 
ያለአቅማችን ጉልበተኛ ነን ማለትም ሆነ ጉልበተኛ ሆነን ምስኪን ኮሳሳ ነን ማለትም ያው መዋሸት ነው፡፡ እያየን አላየንም፣ እየሰማን አልሰማንም፣ እያጠፋን አላጠፋንም ማለትም ያው መቅጠፍ ነው!ያብዬን እከክ ወደ እምዬ ልክክም ያው መዋሸት ነው!ካፈርኩ አይመልሰኝ ማለትም ያው መዋሸት ነው!
Image may contain: text
አስገድደን የምንፈፅመውም ሆነ ዋሽተን የምናሳምነው፣ አሊያም በገንዘብ የምንደልልው፤ የዘወትሩን ሰው ቢያስጨበጭብልንም የክቱን ሰው ያሳዝናል፡፡ በመዋሸት የተገነባ አመኔታ ከጥርጣሬ የፀዳ አይሆንም፡፡ በየፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ ጉዳያችን አንፃር የሌለንን አለን፣ ያለንን የለንም ብለን ከዋሸንና ካሳመንን፤ ተከታያችን ሊደሰትበት፣ አልፎም ሊኮራበት ይችላል፡፡ ያም ሆኖ እንደማናቸውም ነገር ውሸትም ከጥቅም ውጪ የሚሆንበት ጊዜ አለው፡፡
 
የታረዱና የሞቱ ባሉበት አከባቢ የሄዱ የመንግስት ባለስልጣናት ጥቃት የደረሰባቸውን ተጎጂዎችና ሐዘንተኞች ተፈናቃዮች ሳይጎበኙና ሳያጽናኑ ተመልሰዋል። ለምን ይህን አደረጉ ፧ የጉዟቸው አላማ ፖለቲካቸውን ከኪሳራ ማዳን ብቻ ነው።
 
ኦዴፓ ስልጣን ከእጄ እንዳይወጣ በሚል ስጋት በየቦታው ስብሰባ እየጠራ ነው።ግጭት ሲሆን ጥቃት፤ ጥቃት ሲሆን ግጭት እያሉ ሕዝብን ለማምታታት የሚሞክሩ አካላት ያሉት በዚያው በጠቅላዩ ጉያ ነው። የታረዱና የሞቱ ዜጎችን በተመለከተ ምንም ዴንታ ያልሰጠውና ተዘዋውሮ ለማጽናናት ያልፈለገው መንግስት በከፍተኛ ባለስልጣናት ተከፋፍሎ ፖለቲካው ከእጁ እንዳይወጣ ስብከቱን ተያይዞታል። (ምንሊክ ሳልሳዊ)