ፌደራሊዝም በህዝቦች መካከል ከፍተኛ ጉዳት መቃቃርንና ግጭቶችን ፈጥሯል ተባለ

ፌደራሊዝም ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል መባሉ

DW : ተሳታፊዎች አንደገለፁት በአገራችን አለ የተባለው ፌደራሊዝም በህዝቦች መካከል ከፍተኛ ጉዳት መቃቃርንና ግጭቶችን ፈጥሯል፡፡አንድ ተሳታፊ አንዳሉት ፌደራሊዝም በአንዳንድ ክልሎች መካከል ያለው ግንኙነት በአገሮች መካከል ያለ ልዩነት አስመስሎ የሚታይበትን ሁኔታን ምሳሌ በመጥቀስ አብራርተዋል፡፡

ቪዥን ኢትዮጵያ ኮንግረስ ፎር ዲሞክራሲ የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት “ብሔር ተኮር ፌደራሊዝምና ተግዳሮቶች በኢትዮጵያ” በሚል ርዕሰ ዛሬ በባህር ዳር ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ የተገኙ ተሳታፊዎች አንደገለፁት በአገራችን አለ የተባለው ፌደራሊዝም በህዝቦች መካከል ከፍተኛ ጉዳት መቃቃርንና ግጭቶችን ፈጥሯል፡፡

አንድ ተሳታፊ አንዳሉት ፌደራሊዝም በአንዳንድ ክልሎች መካከል ያለው ግንኙነት በአገሮች መካከል ያለ ልዩነት አስመስሎ የሚታይበትን ሁኔታን ምሳሌ በመጥቀስ አብራርተዋል፡፡ ሌላው አስተያየት ሰጪ ደግሞ ፌደራሊዝም የብሔር አክራሪነትን ከማስፋፋቱና ከማጠናከሩ ውጭ የፈጠረው ፋይዳ እንደሌለ ነው ያመለከቱት፡፡

እኝሁ አስተያየት ሰጪ እንደሚሉት ምንም ስያሜ ይሰጠው ፌደራሊዝም በኢትዮጵያ አልነበረም ነው ያሉት፡፡ ለችግሮች ሁሉ መነሻው ፌደራሊዝም የተዋቀረባቸው መነሻዎች መሆናቸው እንደሆነ በእለቱ ጥናታዊ ጽሁፍ ያቀረቡትና በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህሩ አቶ ተገኝ ዘርጋው ናቸው፡፡ የፌደራሊዝም አንቅፋቶች ያሏቸውንም ዘርዝረዋል፡፡

የቪዥን ኢትዮጵያ ኮንግረስ ፎር ዲሞክራሲ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታደለ ደርሰህ ህዝቦች በሰከነ መንገድ ያሉትን ችግሮች በጋራ በመፍታት የዜጎቻችን ስቃይ ማስቆም ገባል ብለዋል፡፡ በውይይቱ ከዩኒቨርሲቲዎች፣ ከሲቪክ ማህበራት፣ ከሐይማኖት አባቶች፣ ከፖለቲካ ድርጅቶችና ከሌሎችም የማህበረሰቡ ክፍሎች ተዉጣጡ አካላት ተገኝተዋል፡፡


► መረጃ ፎረም - JOIN US