ጃዋርና የአብይ ኦዴፓ ድራማ እየሰሩ ነው።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ

Image may contain: one or more people, people standing, people walking and outdoor

ካልደፈረሰ አይጠራም !!! ( ድራማ ??? ) ጃዋር በመንግስተ ኮማንዶዎች ተከቧል። ኦዴፓና ጃዋር ትኩሳት ለመለካት ያቀናጁት ድራማ እንዳይሆን ያጠራጥረኛል። ሰውየው ሩሲያ መሄዱን ተከትለው የኦሮሞ ጽንፈኞቹና የውሕደቱ ተቃዋሚዎች መፈንቅለ መንግስት አድርገው ይሆን ብሎ ማሰብም ሌላኛው የፖለቲካ ጥርጣሬ ነው።የሰሞኑን ቄሮ የፈጠረን ሽብርና ወከባ ተከትሎ በመንግስት ላይ የሕዝብ እና የፖለቲከኞች ጫና ስለበዛ በጃዋር አከባቢ ያለውን የተከማቸ ኃይል ለማሳየት ጥያቄ ባበዙት ብዙሃን ላይ ፍራቻ ለመልቀቅ የታቀደ ሴራም ሊሆን ይችላል። መጠራጠር ይበጃል፤ የኢትዮጵያ ፖለቲካ በሴራ የተሞላ ነው። ድራማው ቀጥሏል ።

መንገድ የመዝጋቱ ሂደት አዲስ አበባ ደረሰ በዚህ ሰዓት ከጀሞ ቁጥር ፪ ወደ አዲስ አበባ ያለው መንገድ ተዘግቶ ሕዝቡ የመንግስት ያለህ እያለ ነው። በካራ በኩል ዞረው ለመግባት የሞከሩትን ደግሞ ፖሊስ አስወርዶ እየፈተሸ ነው። አደገኛ አካሔድ እንዳይሆን ጥንቃቄ ያስፈልጋል ! መንግስት እንደሰማንለት እያደረገ ከሆነ በደንብ ተዘጋጅቷል ማለት ነው ። ለአጀንዳና የሕዝብን አፍ ለማስያዝ ከሆነ ግን በስሜት ለሚደርሱ ጥፋቶች መንግስት ተጠያቂ ነው።

Image may contain: one or more people, people standing and outdoor

ጠባቂዎች  የጅዋርን ጊቢ ለቃቹ ውጡ ተብለዋል። ጃዋር የድረሱልኝ ጥሪ እያሰማ ነው! ራሱ ፌስቡክ ላይ ፅፏል። የስልክ ንግግሮችንም ይፋ አድርጓል።

እንዲህም ሲል ፅፏል ፦ ( ጉዳዩ ለሚመለከተው ሁሉ – በብዛት ወደ መኖሪያዬ እየተሰማራ ያለው የታጠቀ ሀይል ወደኋላ እንዲመለስ በአጽኖት እንጠያቀለን። ማንኛውም ታጥቆ በዚህ ጭለማ ወደግቢ የሚንቀሳቀስ ግለስብም ሆነ ቡድን ላይ ጥበቃው የመከላከል እርምጃ እንደሚወስድ ሊታወቅ ይገባል። ለሚከሰትው ግጭት እና ጉዳት ሙሉ ሀለፊነቱን የሚወስደው ያላንዳች ምክናያት እና ማሳሰቢያ ሀይል ያሰማራው አካል መሆኑን ህዝቡ እንዲያውቅልን እንፈልህጋለን። Jawar Mohammed )

የጃዋር መሐመድ መኖሪያ ቤት አከባቢ ያለው ሁኔታ ይህን Photo ይመስላል። የኦሮሚያ ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች ከጃዋር ጋር አብረው እንዳሉና ለደህንነቱም ጥበቃ ተገቢ እየተደረገለት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል : ድራማው ቀጥሏል ።#MinilikSalsawi