ከጁቡቲ የተነሱ ታጣቂ ሠርጎ ገብ አሸባሪዎች በአፋር ክልል ጥቃት አደረሱ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Image may contain: 1 person, sittingየኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ የጅቡቲ ጦር የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግሮ ጉዳት አድርሷል የሚባለው ወሬ ሐሰት መሆኑን አስታውቋል፡፡

በትናንትናው እለት ከጁቡቲ ሠርጎ ገቦች አሸባሪዎች በአፋር ክልል በአፋምቦ ወረዳ በተኙበት ጨለማን ተገን በማድረግ በአፋር አርብቶ አደሮች በአሸባሪዎች ጥቃት ከደረሰባቸው ህፃናት መካከል ከሞት የተረፉት በርካታ ህፃናት መካከል በአሁኑ በዱቡቲ ሆስፒታል ህክምና እየተሰጣቸው ይገኛል። የሚገርመው ግን ጧቱ ላይ አርብቶ አደሮች መልሱ በማጥቃት በከፈቱት ጦርነት አሸባሪዎች በርካታ የፈረንሳይ ጦር መሳሪያ በመማረክ ከሟቾቹ በርካታ የሠነድ ማስረጃዎችን በቁጥጥራቸው ሥር ሊያደርጉ ችለዋል። አሁን የአፋር ህዝብን እየገደለ የሚገኘው ከጎረቤት አገራት የሚገቡ ሠርጎ ገቦች ናቸው።

ከአፄው ዘመነ መንግስት ጀምሮ እስከ ዶክተር አብይ መንግስት ድረስ አፋርን ከበስተጀርባ ሆኖ የራሱን አለማ ለማሳከት እየጨፈጨፈ የሚገኘው የጎረቤት አገራት ፖለቲካ ጠልቃ ገብነት ነው።

በዛ ልክ በኮንትሮባንድ ንግድ ላይ የተሰማሩ ከሚኒንስተር እስከጦር አመራር ያሉ የኢትዮጵያ የማአከላዊ መንግስት አመራሮች ሴራና ለሐብት ማካበት የሚደረገው ጥረት ውጤት ነው። ሚስኪኑ የኢሳና አፋር አርብቶ አደሮች ግን ፍዳቸውን እየከፈሉ ነው። ኢሳና አፋር የግጭቱን መንስኤ የሚፈቱበት አኩራ ባህል አሏቸው።

ይሁን እንጅ ሰከን ብለው ጉዳዮቻቸውን እንዳይመለከቱ የሚያደርጉ የፖለቲካ ቅብብሎሽ የሚጫወቱ የኮንትሮባንድ ነጋዴዎች ስላሉ አፋርና ኢሳ ዘመን ተሻጋሪ ጠላት እንዲፈራራጁ አድርጎታል። የእምነት ወንድማማቾች ግን በሚያሳዝን ሁኔታ እልቂት በመካከላቸው እየተፈጠረ ይገኛል። የፌዴራል መንግሰት የድራማው አካል ነው። ይህ ባይሆን ኑሮማ በየግዜው የተለያዩ አስረጂ ማስረጃዎች ከጁቡቲም ፣ከሱማሌም ለዶክተር አብይ እየቀረቡለት ከፋርማጆ ጋር በቤተመንግስታቸው ተቃቅፈው በሳቅ በልፈነደቁ ነበር።

Image may contain: 1 person, sittingከጁቡቲ መሪ ጋር በዛው ልክ ባልተራመዱ ነበር። የፊቱን ትተን በትናንትናው እለት በኦብኖ ህፃናትና ሴቶችን በዘርመጥፋት አይነት ዘመቻ የተፈፀመው ጭፍጨፋ ከ40 የሚሆኑ የሠርጎ ገቦች ማስረጃ ከእነጦር ትጥቃቸው ፣ ከመላያ መታወቂያ ጋር ተሰብሰቦ በአፋር አመራሮች እጅ ይገኛል። ብዙዎቹም የሱማሌ ልዩሐይሎች ናቸው። ልክ እንደትናንቱ አሁንም መረጃውን በህይወት ከተያዙም ጭምር ለመንግስት በአስረጂነት እናቀርባለን። ይህ ህፃን በተኛበት በሠርጎ ገቦች በተቶኮሰ ጥይት በጭቅላነቱ ገና ያላደገ ሠውነቱ ተከትክቶ አጥንቱን ሰብሮ አስቃቂ ህመም እንዲጋፈጠው አድርጎታል።

አብሮ አደጎቹና ወንድሞቹ ግን በጥፋት ሐይሎች በተቶኮሰ ጥይት የተስፋ ህይወታቸው ተቀጭቶ ላይመለሱ በእንቅል አላም ላይ እያሉ ዳግም ላይመለሱ አሸልበው የመኖር ተስፋቸው ተቀጭተዋል። ይህ ነው እንግዲህ ነባራዊ ሁኔታ። የፌዴራል መንግስት የአፋርን ህይወት መታደግ አልቻለም። ከዚህ ቡሗላ የቀረው ነገር ቢኖር የአፋር ህዝብ ራሱን በራሱ ሐላፊነት በተሞላበት መልኩ የክልሉ መንግስት የቀጠናው ሠላም ለማስከበር ከሁሉ በፊነት ነቆና ተደራጅቶ የጥፋት ሐይሎችን መመከት አለበት ግጭቱ የኢሳና አፋር ግጭት አይደለምና። የግጦሽና የውሃ ግጭት ነው የሚለው የኮንትሮባንዲስቶች የማደንዘዣ ድራማ ግዜው አልፎበታል።

የውጭ ሐይሎችና የኮንትሮባንድ ንግድ ባለሐብቶች ከአፋርና ኢሳ ጉዳይ እጃቸውን ሲያወጡ ያኔ አፋርና ኢሳ አብረው በሠላም ተግባብተው ተቻችለው መኖርን በራሳቸው መንገድ ምርጫ አድርገው አብረው በፍቅር መኖርን ይጀምራሉ።

Allo Yayo Abu Hisham / Afar Media

Image may contain: one or more people, people sitting and people sleeping

በአፋር ክልል አፋምቦ ወረዳ ሜጉ ቀበሌ የታጠቁ ኃይሎች በፈፀሙት ጥቃት የ16 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

ጥቃቱ የተፈፀመው ቅዳሜ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽት ድረስ መሆኑን የአፋር ክልል የወንጀል መከላከል ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አህመድ ኡመድ ለኢቢሲ ተናግረዋል።

በጥቃቱ እስካሁን 16 የሚሆኑ ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ከእነዚህም መካከል 3ቱ ህፃናት እና 4ቱ ደግሞ ሴቶች ናቸው ብለዋል።

ጥቃቱ በተሸከርካሪ የታገዘ እንደነበረ የተገለፀ ሲሆን የሰነድ ማስረጃዎችን ማግኘት እንደተቻለም ነው ም/ል ኮሚሽነሩ የተናገሩት፡፡

በጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸው በርካታ ህፃናት በዱቡቲ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ነው ተብሏል።

የኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ የጅቡቲ ጦር የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግሮ ጉዳት አድርሷል የሚባለው ወሬ ሐሰት መሆኑን አስታውቋል፡፡

“የጅቡቲ ጦር የኢትዮጵያን ድንብር ተሻግሮ በአፋር በኩል ዜጎች ላይ ጉዳት አደረሰ” የሚለው ወሬ ሐሰት መሆኑን በመከላከያ ሚኒስቴር የምክትል ኤታማዦር ሹም ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኮሎኔል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ ተናግረዋል።