" /> የተደራጁ አካላት የመንግስትን እጅ በመጠምዘዝ ሕግና ፍትሕን በራሳቸው መንገድ እያስፈጸሙ ነው | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

የተደራጁ አካላት የመንግስትን እጅ በመጠምዘዝ ሕግና ፍትሕን በራሳቸው መንገድ እያስፈጸሙ ነው

ከመቼውም ግዜ በባሰ ሁኔታ የሕግ የበላይነት የሚባለው ነገር ሀገሪቷ ላይ ድምጥማጡ ጠፍቷል። ከዚህ ቀደም በአብዛኛው የሕግ የበላይነትን ሲፃረር የምናየው የመንግስት interest አለበት በተባሉና ከመንግስት ባለስልጣኖች ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ነበር።

አሁን ግን በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ የተደራጁ አካላት ሕግ እና ፍትሕን በራሳቸው መንገድ ሲያስፈፅሙ እያየን ነው። በቀደም በደብረብርሃን የታሰሩ ቄሮዎች ካልተፈቱ መንገዱን አንከፍትም ያሉ ውርጋጦች ጥያቄያቸው ተመልሶ መንገዱን ከፈቱ።

ትላንት ደሞ በአዲስ አበባ ፖሊስ በተለያየ ነገር ጠርጥሬያቸዋለሁ ብሎ ባለፈው ሀሙስ ያሰራቸውን ግለሰቦች ፍ/ቤት የሁለት ቀን ጊዜ ቀጠሮ ሰጥቶ ሳለ የሙስሊም መፍትሔ ኮሚቴ አፈላላጊ አካላት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን በማነጋገር አስፈቱ።

ጥያቄው መንግስት በዚህ ደረጃ ወርዶ በተደራጁ አካላት እጁ የሚጠመዘዝ ከሆነ ሕግ ፣ ፍርድ ቤት ፣ የፍትሕ አካላት የሚባሉት ነገሮች ፋይዳቸው ምንድን ነው? ፍርድ ቤቶች የሕግ የበላይነትን የማስከበር አቅማቸውን በዚህ ደረጃ እንዴት ይነጠቃሉ? #NatnaelTeklu


የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV