ከዳካር-ባማኮ-አዲስ አበባ ይበር የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ባጋጠመው የቴክኒክ እክል ምክንያት ሴኔጋል አረፈ


ኢትዮጵያን ካጋጠሟት እጅግ ውስብስብ ችግሮች ለማዳን የተለያዩ ጠቃሚ ሃሳቦችን እና ገንቢ ትችቶችን የሚያቀርቡ ነፃ ሚዲያዎች ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ይታወቃል። ስለዚህም ኢትዮ360፣ መረጃ ቲቪ፣ አዲስ ድምጽ፣ ምንሊክ ቲቪ እና ሌሎችም የኢትዮጵያዊነት አጀንዳ የሚያራምዱ ሚዲያዎች በመተባበር ፕሮግራሞቻቸውን በሳተላይት ቲቪ ለኢትዮጵያ ህዝብ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ሚዲያዎች የፈጠሩት ማህበር የሳተላይት ወጪውን መሸፈን እንዲያስችለው ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ ከፍተናል → እዚህ ሊንክ ላይ ይጫኑ። ለትብብርዎ እናመሰግናለን።

ከዳካር-ባማኮ-አዲስ አበባ ይበር የነበረው ንብረትነቱም የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነው የበረራ ቁጥር ET-908 አውሮፕላን ባጋጠመው የቴክኒክ እክል ምክንያት እዛው ሴኔጋል ለማረፍ መገደዱ ተሰማ። B767-300 አውሮፕላን በመደበኛ በረራ ከሴኔጋል ዲአስ በማሊ ባማኮ አድርጎ አዲስ አበባ ለመብረር ጉዞ ጀምሮ ነበር ተብሏል።

የበረራ ቁጥር ET-908 ባጋጠመው የቴክኒክ እክል ምክንያት ወደተነሳበት ኤርፖርት ተመልሶ ለማረፍ መገደዱንም በአውሮፕላኑ የነበሩ መንገደኞችም በሌላ አውሮፕላን ተሳፍረው ጉዞዋቸውን ቀጥለዋል ተብሏል።የኢትዮጵያ አየር መንገድም ለተፈጠረው መጉላላት መንገደኞቹን ይቅርታ ጠይቋል።አውሮፕላኑ ስላጋጠመው የቴክኒክ እክልም እንዲህም ነው እንዲያም ነው የተባለ ነገር የለም።

Image

Ethiopian Airlines plane makes emergency landing in Senegal

An Ethiopian Airlines plane was on Tuesday forced to make an emergency landing at the Blaise Diagne International Airport in Diass, Senegal, after developing a technical problem, the airline confirmed.

Read More : https://africa.cgtn.com/2019/10/08/ethiopian-airlines-plane-makes-emergency-landing-in-senegal/

Image