" /> የአማራ ክልልን ሰላምና ጸጥታ ለማወክ አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን የጀመሩትን ዘመቻ እንዲያቆሙ ተጠየቀ | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

የአማራ ክልልን ሰላምና ጸጥታ ለማወክ አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን የጀመሩትን ዘመቻ እንዲያቆሙ ተጠየቀ

አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን ተቋማት የአማራ ክልልን ሰላምና ፀጥታ ለማወክ የጀመሩትን ዘመቻ እንዲያቆሙ ተጠየቀ

አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን የአማራ ክልልን ሰላምና ጸጥታ ለማወክ የጀመሩትን ዘመቻ በአፋጣኝ እንዲያቆሙ አመራሮች ጠየቁ።

የብሮድካስት ባለስልጣን ችግሩን ለመፍታት ለመገናኛ ብዙሃኑ ሙያዊ እገዛ እንደሚያደርግ ገልጿል።

የአገሪቷ የለውጥ ሂደት ከታገለባቸው ጉዳዮች መካከል የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት አንዱ ነው።

በዚህም በአሸባሪነት ጭምር ተፈርጀው የነበሩና በአገር ውስጥ እንዳይሰሩ የተከለከሉ አንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ጭምር በነፃነት እንዲሰሩ ፍቃድ የተሰጣቸው መሆኑንም አስተያየት ሰጪዎቹ ገልጸዋል።

ይሁንና ነጻነታቸውንና ሃላፊነታቸውን ባላጣጣመ መልኩ የአማራ ክልልን ሰላምና ጸጥታ የሚያደፈርሱና ከእውነት የራቁ መረጃዎችን የሚያሰራጩ አንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል ነው ያሉት።

የብሮድካስት ባለስልጣን በበኩሉ የብሮድካስት አዋጁን በሚጻረር መልኩ መረጃ የሚያሰራጩ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት መኖራቸውን አምኗል።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጌታቸው ድንቁ መገናኛ ብዙሃን የተሰጣቸውን ነጻነት በሃላፊነት መንፈስ ሊጠቀሙ እንደሚገባ ለኢዜአ ተናግረዋል።

www.ena.et/?p=63648


የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV