ሕዝብን ዝም ለማሰኘትና ፍርሐት ለመልቀቅ የተነደፈው ሽብርና የጥላቻ ዲስኩር ሊቆም ይገባል።

Image may contain: one or more people, people walking, people standing and outdoor

ሕዝብን ዝም ለማሰኘትና ፍርሐት ለመልቀቅ የተነደፈው ሽብርና የጥላቻ ዲስኩር ሊቆም ይገባል።(ምንሊክ ሳልሳዊ)

Image may contain: one or more people, people standing, people walking and outdoor

የሐገርንና የሕዝብን ሰላም እየነሳ ያለው መንግስታዊ መዋቅሩና በጉያው የታቀፋቸው ዘረኞች ናቸው ብለን መጮኽ ከጀመርን ቆየን።መንግስታዊ መዋቅሩ ውስጥ ያሉት የመንግስት ባለስልጣናትና በእቅፎቻቸው ያሉ ዘረኞች ጥላቻ እየነዙ ሰላምን እያደፈረሱ ነው። ይህንንም በሸኖ በአጣዬና ድሬደዋ እያየነው ነው።

በሸኖ ከግሸን ደብረ ከርቤ ሐይማኖታዊ በዓል የሚመለሱ ምእመናንና በአጣዬና ድሬደዋ በሰላም የሚኖሩ ነዋሪዎችን በማሸበር ተግባር ላይ የተሰማሩ የመንግስት ሰዎችና የጥላቻ አራማጆች እጃቸውን ከሰላማዊ ሕዝብ ላይ ሊያነሱ ይገባል።ዜጎች በገዛ ሐገራቸው ተዘዋውረው የመኖር መብት እንዳላቸው መንግስት ሊያውቅ ይገባል።

Image may contain: car and outdoor

ከግሸን ደብረ ከርቤ ክብረ በአል ተመላሾች በአሁኑ ሰአት ሸኖ ላይ ከፊትም ከኃላም መንገድ ተዘግቶባቸው ቆመዋል፤ ከእሬቻ ክብረ በዐል ሲመለሱ ደብረ ብርሃን የታሰሩ ወጣቶች ካልተፈቱ መንገዱን አንክፍትም ተብለዋል፤ደብረብርሃን ላይ የታሰሩት ከወራት በፊት ኬሚሴ እና አጣዬ ላይ ጥቃት እንዲፈፀም ያደረጉ የታጣቂው ኦነግ አመራሮች ናቸው። እነዚህ ሶስት አመራሮች ማደኛ ሲወጣባቸው ተደብቀው ወለጋ ከርመዋል። በቅርቡ ለኢሬቻ በሚል በኬሚሴ በኩል ሲመጡ የኬሚሴ አመራሮች ጠቁመው አስይዘዋቸዋል።

Image may contain: sky, outdoor and nature

አጣዬ የተፈጠረው ተኩስና አለመረጋጋት አሁንም እንደቀጠለ ነው። ሁኔታዎች ወደከፋ ደረጃ እንዳይደርሱ መንግስት የባለስልጣናቱን የሽብር እጆች በመሰብሰብ መፍትሄ መፈለግ አለበት፤ ችግሩም የመንግስት ልዩ ትኩረት ይሻል።

ዛሬ በጠዋቱ ቄሮ ናቸው የተባሉ ኦሮሞ ወጣቶች በአይሱዙ መኪና ተጭነው ወደ ድሬደዋ ሲገቡ የፅጥታ ኃይሉ ሁኔታውን ተከታትሎ ችግሩ ሳይፈጠር ማስቆም ይችል ነበር።

በአይሱዙ የገቡት ወጣቶች ደቻቱ ሰፈር ችግር መፍጠር ሲጀምሩ (እንደ ነዋሪዎቹ ከሆነ መደብሮችን መዝረፍ እና ያገኙትን መደብደብ ሲጀምሩ) የድሬዳዋ ወጣት ከተማዋን ለመከላከል ጥረት አድርገዋል። መጀመርያ በአይሱዙ ተጭነው ገብተው ከተማውን ለመበጥበጥ ሲጥሩ ዝምታን የመረጠው የፀጥታ ኃይል የድሬዳዋ ወጣቶች ከተማዋን ለመጠበቅ ሲጥሩ ግን ፈጥኖ ደርሷል።ሁኔታዎች ወደከፋ ደረጃ እንዳይደርሱ ልዩ ትኩረት ይሻል። #MinilikSalsawi