70 የፖለቲካ ፓርቲዎች የረሃብ አድማ ሊያደርጉ መሆኑን ገለጹ

[addtoany]

Sheger FM : “የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ያቀረብነውን የተቃውሞ ድምጽ ካልተመለከተ የረሃብ አድማ ለ2 ቀናት እናደርጋለን” ሲሉ የ70 የፖለቲካ ፓርቲዎች አስተባባሪ ኮሚቴ ተናገረ፡፡

የ70 የፖለቲካ ፓርቲ አስተባባሪ ኮሜቴ ነን ያሉ ፖለቲከኞች በመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ፅህፈት ቤት በሰጡት መግለጫ፣ የፀደቀውን የፖለቲካ ፓርቲዎች አሰራር እና ምዝገባ አዋጅን በመቃወም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጭምር ተቃውሞ ብናቀርብም ሰሚ በማጣታችን የረሃብ አድማ ልናደርግ ነው ብለዋል፡፡

የረሃብ አድማችን በተመሳሳይ ሰሚ ካጣ በመላው ኢትዮጵያ አዋጁን የሚቃወም የፊርማ ማሰባሰብ ሥራ ውስጥ እንገባለን ሲሉ ተናግረዋል..